Loading...
Language: Amharic
በጠዋት ወይም በማታ ይበሉ -
اَللَّهُمَّ عَالِمَ الْغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ فَاطِرَ السَّمَوَاتِ وَالْأَرْضِ، رَبَّ كُلِّ شَيْءٍ وَمَلِيكَهُ، أَشْهَدُ أَنْ لَا إِلَهَ إِلَّا أَنْتَ، أَعُوْذُ بِكَ مِنْ شَرِّ نَفْسِي، وَمِنْ شَرِّ الشَّيْطَانِ وَشِرْكِهِ ، وَأَنْ أَقْتَرِفَ عَلَى نَفْسِي سُوْءًا، أَوْ أَجُرَّهُ إِلَى مُسْلِمٍ
አላሁመ አሊመል-ገይቢ ወሽ-ሸሀደቲ ፋጢረስ-ሰማዋቲ ወል-አርድ፣ ረበ ኩሊ ሸይኢን ወ መሊከሁ፣ አሽሀዱ አን ላ ኢላሀ ኢላ አንተ፣ አዑዙ ቢከ ሚን ሸሪ ነፍሲ፣ ወ ሚን ሸሪሽ-ሸይጣኒ ወ ሺርኪሂ፣ ወ አን አቅተሪፈ አላ ነፍሲ ሱአን፣ አው አጁረሁ ኢላ ሙስሊም።
አላህ ሆይ! የሩቁንም የቅርቡንም አዋቂ፣ የሰማያትና የምድር ፈጣሪ፣ የሁሉም ነገር ጌታና ንጉስ፣ ከአንተ በስተቀር በእውነት የሚመለክ (አምላክ) እንደሌለ እመሰክራለሁ። ከነፍሴ ክፋት፣ ከሰይጣን ክፋትና ከሽርኩ፣ በነፍሴ ላይ ክፉን ከመፈጸም ወይም ወደ ሌላ ሙስሊም ከማምጣት (ከመሳብ) በአንተ እጠበቃለሁ። አቡ በክር አስ-ሲዲቅ (ረ.ዐ) እንዲህ አሉ፡- «የአላህ መልእክተኛ ሆይ፣ በጠዋት እና በማታ የምለውን አስተምሩኝ።» እሳቸውም፡- «አቡ በክር ሆይ፣ (ይህንን ከላይ ያለውን ዱዓ) በል።» አሉ።
Reference: ሰሂህ (አልባኒ)። ቲርሚዚ፡ ፴፭፻፳፱