Loading...
Language: Amharic
በጠዋት (እና በማታ) ይበሉ፣
اَللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ الْعَفْوَ وَالْعَافِيَةَ فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ، اَللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ الْعَفْوَ وَالْعَافِيَةَ فِي دِينِيْ وَدُنْيَايَ وَأَهْلِيْ، وَمَالِيْ، اَللَّهُمَّ اسْتُرْ عَوْرَاتِيْ، وَآمِنْ رَوْعَاتِيْ، اَللَّهُمَّ احْفَظْنِي مِنْ بَيْنِ يَدَيَّ وَمِنْ خَلْفِي وَعَنْ يَمِيْنِيْ وَعَنْ شِمَالِي وَمِنْ فَوْقِيْ وَأَعُوْذُ بِعَظَمَتِكَ أَنْ أُغْتَالَ مِنْ تَحْتِيْ
አላሁመ ኢንኒ አሰአሉከል-አፍወ ወል-አፊየተ ፊድ-ዱንያ ወል-አኺራ፣ አላሁመ ኢንኒ አሰአሉከል-አፍወ ወል-አፊየተ ፊ ዲኒ ወ ዱንያየ ወ አህሊ፣ ወ ማሊ፣ አላሁመ-ስቱር አውራቲ፣ ወ አሚን ረውአቲ፣ አላሁመ-ህፈዝኒ ሚም በይኒ የደየ፣ ወ ሚን ኸልፊ፣ ወ አን የሚኒ፣ ወ አን ሺማሊ፣ ወ ሚን ፈውቂ፣ ወ አዑዙ ቢ-አዘመቲከ አን ኡግታለ ሚን ተህቲ።
አላህ ሆይ፣ እኔ በዱንያ እና በአኺራ ይቅርታን እና ደህንነትን እጠይቅሃለሁ። አላህ ሆይ፣ እኔ በሃይማኖቴ እና በዱንያ ጉዳዮቼ፣ በቤተሰቤ እና በንብረቴ ይቅርታን እና ደህንነትን እጠይቅሃለሁ። አላህ ሆይ፣ ነውሬን ሸፍንልኝ፣ ፍርሃቴንም አረጋጋልኝ። አላህ ሆይ፣ ከፊቴ እና ከኋላዬ፣ ከቀኜ እና ከግራዬ፣ ከላዬም ጠብቀኝ፤ ከስሬ እንዳልዋጥም በታላቅነትህ እጠበቃለሁ። አብዱላህ ኢብን ኡመር (ረ.ዐ) እንዳሉት፣ የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) እነዚህን ዱዓዎች በማታ እና በጠዋት ፈጽሞ አይተዋቸውም (አይረሷቸውም) ነበር።
Reference: ሰሂህ (አልባኒ)። አቡ ዳውድ፡ ፶፻፸፬