Loading...
Language: Amharic
የኃጢአት ምህረት ከአላህ ሊጠየቅ ይገባል፤ ምክንያቱም አንድ ባሪያ ጌታውን ሊጠይቀው የሚችለው እጅግ አስፈላጊ ነገር ለኃጢአቱ ምህረትን ወይም የማይቀረውን ውጤቱን (ቅጣቱን) ነው። ለምሳሌ ከገሃነም መዳንን እና ወደ ጀነት መግባትን። ባሪያው ከጌታው ለኃጢአቱ ምህረትን ይፈልጋል፤ ምክንያቱም በየቀኑ እና በየሌሊቱ ስህተቶችን ይሠራልና፤ ሁሉንም ኃጢአቶች መማር የሚችለው አላህ ብቻ ነው። የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ልቤ ግድየለሽነት ይውጠዋል፤ እኔም በቀን መቶ ጊዜ የአላህን ይቅርታ እጠይቃለሁ።
Reference: ሰሂህ (አልባኒ)። አቡ ዳውድ፡ ፲፭፻፲፭