Loading...
Language: Amharic
የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-
بِسْمِ اللَّـهِ الرَّحْمَـٰنِ الرَّحِيمِ اَلْحَمْدُ لِلَّـهِ الَّذِي أَنزَلَ عَلَىٰ عَبْدِهِ الْكِتَابَ وَلَمْ يَجْعَل لَّهُ عِوَجًا ۜ ﴿١﴾ قَيِّمًا لِّيُنذِرَ بَأْسًا شَدِيدًا مِّن لَّدُنْهُ وَيُبَشِّرَ الْمُؤْمِنِينَ الَّذِينَ يَعْمَلُونَ الصَّالِحَاتِ أَنَّ لَهُمْ أَجْرًا حَسَنًا ﴿٢﴾ مَّاكِثِينَ فِيهِ أَبَدًا ﴿٣﴾ وَيُنذِرَ الَّذِينَ قَالُوا اتَّخَذَ اللَّـهُ وَلَدًا ﴿٤﴾ مَّا لَهُم بِهِ مِنْ عِلْمٍ وَلَا لِآبَائِهِمْ ۚ كَبُرَتْ كَلِمَةً تَخْرُجُ مِنْ أَفْوَاهِهِمْ ۚ إِن يَقُولُونَ إِلَّا كَذِبًا ﴿٥﴾ فَلَعَلَّكَ بَاخِعٌ نَّفْسَكَ عَلَىٰ آثَارِهِمْ إِن لَّمْ يُؤْمِنُوا بِهَـٰذَا الْحَدِيثِ أَسَفًا ﴿٦﴾ إِنَّا جَعَلْنَا مَا عَلَى الْأَرْضِ زِينَةً لَّهَا لِنَبْلُوَهُمْ أَيُّهُمْ أَحْسَنُ عَمَلًا ﴿٧﴾ وَإِنَّا لَجَاعِلُونَ مَا عَلَيْهَا صَعِيدًا جُرُزًا ﴿٨﴾ أَمْ حَسِبْتَ أَنَّ أَصْحَابَ الْكَهْفِ وَالرَّقِيمِ كَانُوا مِنْ آيَاتِنَا عَجَبًا ﴿٩﴾ إِذْ أَوَى الْفِتْيَةُ إِلَى الْكَهْفِ فَقَالُوا رَبَّنَا آتِنَا مِن لَّدُنكَ رَحْمَةً وَهَيِّئْ لَنَا مِنْ أَمْرِنَا رَشَدًا ﴿١٠﴾
ቢስሚላሂር ረህማኒር ረሂም። አልሀምዱ ሊላሂለዚ አንዘለ ዐላ ዐብዲሂል ኪታበ ወለም የጅዐል ለሁ ዒወጃ። ቀይይመል ሊዩንዚረ ባእሰን ሸዲደም ሚን ለዱንሁ ወዩበሽሺረል ሙእሚኒነለዚነ የዕመሉነ ሷሊሀቲ አንነ ለሁም አጅረን ሀሰና። ማኪሲነ ፊሂ አበዳ። ወዩንዚረለዚነ ቃሉ ተኸዘላሁ ወለዳ። ማ ለሁም ቢሂ ሚን ዒልሚን ወላ ሊአባኢሂም፤ ከቡረት ከሊመተን ተኽሩጁ ሚን አፍዋሂሂም፤ ኢን የቁሉነ ኢላ ከዚባ። ፈለዐለከ ባኺዑን ነፍሰከ ዐላ አሳሪሂም ኢን ለም ዩእሚኑ ቢሀዘል ሀዲሲ አሰፋ። ኢንና ጀዐልና ማ ዐለል አርዲ ዚነተል ለሀ ሊነብሉወሁም አዩሁም አህሰኑ ዐመላ። ወኢንና ለጃዒሉነ ማ ዐለይሀ ሰዒደን ጁሩዛ። አም ሀሲብተ አንነ አሻበል ከህፊ ወርረቂሚ ካኑ ሚን አያቲና ዐጀባ። ኢዝ አወል ፊቲየቱ ኢለል ከህፊ ፈቃሉ ረበና አቲና ሚን ለዱንከ ራህመተን ወሀይይእ ለና ሚን አምሪና ረሸዳ።
(1) ምስጋና ለአላህ ይገባው፣ ለዚያ ባሪያው ላይ መጽሐፉን ላወረደው፣ በውስጡም ምንም መጣመምን ላላደረገበት። (2) ቀጥተኛ ሲሆን (አወረደው)፤ ከእርሱ ዘንድ ከሆነው ብርቱ ቅጣት ሊያስፈራራበት፣ እነዚያንም መልካም ስራዎችን የሚሰሩትን አማኞች ለእነሱ መልካም ምንዳ ያላቸው መሆኑን ሊያበስርበት። (3) በእርሱ (በምንዳው) ውስጥ ዘውታሪዎች ሲሆኑ። (4) እነዚያንም «አላህ ልጅን ያዘ» ያሉትን ሊያስጠነቅቅበት። (5) ለእነርሱ በእርሱ (በንግግራቸው) ምንም እውቀት የላቸውም፣ ለአባቶቻቸውም (እንደዚሁ)፤ ከክፉ የሚወጣው ቃል (ንግግር) ከበደች፣ ውሸትን እንጂ አይናገሩም። (6) በዚህ ንግግር (ቁርአን) ባያምኑ በዱካቸው ተከትለህ በሃዘን ነፍስህን ልታጠፋ ይከጅልሃል። (7) እኛ በምድር ላይ ያለን ሁሉ ለእርሷ ጌጥ አደረግን፣ (ሰዎቹን) ማንኛቸው ስራው ይበልጥ ያማረ መሆኑን ልንፈትናቸው። (8) እኛም በእርሷ ላይ ያለን ነገር ሁሉ (መጨረሻ ላይ) ድርቅ መሬት አድራጊዎች ነን። (9) ወይስ የካህፍ (የዋሻ) እና የረቂም (የጽሁፍ) ጓዶች ከምልክቶቻችን አስደናቂ እንደነበሩ ጠረጠርክን? (10) ወጣቶቹ ወደ ዋሻው በተጠጉ ጊዜ፣ «ጌታችን ሆይ! ከአንተ ዘንድ እዝነትን ስጠን፣ ለእኛም ከነገራችን ቀጥታን አዘጋጅልን» ባሉ ጊዜ (አስታውስ)። (ሱረቱል ካህፍ፡ 1-10) ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- «የሱረቱል ካህፍን የመጀመሪያዎቹን አስር አንቀጾች በቃሉ ያጠና፣ ከደጃል ይጠበቃል።»
Reference: ሙስሊም፡ ፰፻፱