Loading...
Language: Amharic
اَللَّهُ لَآ إِلٰهَ إِلَّا هُوَ الْحَىُّ الْقَيُّومُ ۚ لَا تَأْخُذُهُۥ سِنَةٌ وَلَا نَوْمٌ ۚ لَّهُۥ مَا فِى السَّمٰوٰتِ وَمَا فِى الْأَرْضِ ۗ مَنْ ذَا الَّذِى يَشْفَعُ عِنْدَهُۥٓ إِلَّا بِإِذْنِهِۦ ۚ يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ ۖ وَلَا يُحِيطُونَ بِشَىْءٍ مِّنْ عِلْمِهِۦٓ إِلَّا بِمَا شَآءَ ۚ وَسِعَ كُرْسِيُّهُ السَّمٰوٰتِ وَالْأَرْضَ ۖ وَلَا يَـُٔودُهُۥ حِفْظُهُمَا ۚ وَهُوَ الْعَلِىُّ الْعَظِيمُ
አላሁ ላ ኢላሀ ኢላ ሁወል-ሀዩል-ቀዩም፣ ላ ተእኩዙሁ ሲነቱ ን ወላ ነውም፣ ለሁ ማ ፊስ-ሰማዋቲ ወ ማ ፊል-አርድ፣ መን ዘል-ለዚ የሽፈኡ ኢንደሁ ኢላ ቢኢዝኒህ፣ የዕለሙ ማ በይነ አይዲሂም ወ ማ ኸልፈሁም፣ ወላ ዩሂጡነ ቢሸይኢ ም-ሚን ኢልሚሂ ኢላ ቢማ ሻአ፣ ወሲአ ኩርሲዩሁስ-ሰማዋቲ ወልአርድ፣ ወላ የኡዱሁ ሂፍዙሁማ፣ ወ ሁወል-አሊዩል-አዚም።
አላህ ከእርሱ በስተቀር በእውነት የሚመለክ (አምላክ) የለም። ሕያው ራሱን ቻይ ነው። ማንገላጀትም እንቅልፍም አይይዘውም። በሰማያት ውስጥ ያለውና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው። ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢሆን እንጂ የሚያማልድ ማነው? (ከፍጡራን) በፊታቸው ያለውንና ከኋላቸው ያለውን ሁሉ ያውቃል። ከእውቀቱም እርሱ የሻውን እንጂ በምንም ነገር አያካብቡም (አያውቁም)። ወንበሩ ሰማያትንና ምድርን ሰፋ። ሁለቱንም መጠበቅ አያዳክመውም። እርሱም ልዑል ታላቅ ነው። (ሱረቱል በቀራህ 2፡255) ለመተኛት ሲል አያቱል ኩርሲን የቀራ ሰው፣ ከአላህ ዘንድ የሆነ ጠባቂ አብሮት ይቆያል እና እስኪነጋ ድረስ ሰይጣን ሊቀርበው አይችልም።
Reference: አል-ቡኻሪ፣ ፈትሁል ባሪ ፬/፬፻፹፯፣ ቁጥር ፳፫፻፲፩