Loading...
Language: Amharic
آمَنَ الرَّسُولُ بِمَا أُنْزِلَ إِلَيْهِ مِن رَّبِّهِ وَالْمُؤْمِنُونَ ۚ كُلٌّ آمَنَ بِاللَّـهِ وَمَلَائِكَتِهِ وَكُتُبِهِ وَرُسُلِهِ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِّن رُّسُلِهِ ۚ وَقَالُوا سَمِعْنَا وَأَطَعْنَا ۖ غُفْرَانَكَ رَبَّنَا وَإِلَيْكَ الْمَصِيرُ ﴿٢٨٥﴾ لَا يُكَلِّفُ اللَّـهُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَا ۚ لَهَا مَا كَسَبَتْ وَعَلَيْهَا مَا اكْتَسَبَتْ ۗ رَبَّنَا لَا تُؤَاخِذْنَا إِن نَّسِينَا أَوْ أَخْطَأْنَا ۚ رَبَّنَا وَلَا تَحْمِلْ عَلَيْنَا إِصْرًا كَمَا حَمَلْتَهُ عَلَى الَّذِينَ مِن قَبْلِنَا ۚ رَبَّنَا وَلَا تُحَمِّلْنَا مَا لَا طَاقَةَ لَنَا بِهِ ۖ وَاعْفُ عَنَّا وَاغْفِرْ لَنَا وَارْحَمْنَا ۚ أَنْتَ مَوْلَانَا فَانْصُرْنَا عَلَى الْقَوْمِ الْكَافِرِينَ ﴿٢٨٦﴾
(285) አመነር-ረሱሉ ቢማ ኡንዚለ ኢለይሂ ሚር-ረቢሂ ወል ሙእሚኑን፣ ኩሉን አመነ ቢላሂ ወ መላኢከቲሂ ወ ኩቱቢሂ ወ ሩሱሊህ፣ ላ ኑፈሪቁ በይነ አሀዲ ም-ሚር-ሩሱሊህ፣ ወ ቃሉ ሰሚዕና ወ አጠዕና ጉፍራነከ ረበና ወ ኢለይከል-መሲር። (286) ላ ዩከሊፉላሁ ነፍሰን ኢላ ውሰአሀ፣ ለሀ ማ ከሰበት ወ አለይሀ መክተሰበት፣ ረበና ላ ቱአኺዝና ኢን ነሲና አው አኽጦእና፣ ረበና ወላ ተህሚል አለይና ኢስረን ከማ ሀመልተሁ አለል-ለዚነ ሚን ቀብሊና፣ ረበና ወላ ቱሀሚልና ማ ላ ጣቀተ ለና ቢህ፣ ወዕፉ አና፣ ወግፊር ለና ወርሀምና፣ አንተ መውላና ፈንሱርና አለል-ቀውሚል-ካፊሪን።
(285) መልእክተኛው ከጌታው ወደርሱ በተወረደው አመነ፤ አማኞችም (እንደዚሁ)። ሁሉም በአላህ፣ በመላእክቶቹም፣ በመጽሐፎቹም፣ በመልእክተኞቹም አመኑ፤ «ከመልእክተኞቹ በአንድም መካከል አንለይም» (ይላሉ)። «ሰማን ታዘዝንም፤ ጌታችን ሆይ! ምህረትህን (እንሻለን)፤ መመለሻም ወደ አንተ ነው» አሉ። (286) አላህ ነፍስን ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም። ለርሷ (የሰራችው) መልካም ስራ አላት፤ በእርሷም ላይ (የሰራችው) ኃጢአት አለባት። «ጌታችን ሆይ! ብንረሳ ወይም ብንስት አትያዘን (አትቀጣን)። ጌታችን ሆይ! ከባድ ሸክምንም እንደዚያ ከእኛ በፊት በነበሩት ላይ እንደጫንከው በእኛ ላይ አትጫንብን። ጌታችን ሆይ! ለእኛም በእርሱ አቅም የሌለንን ነገር አታሸክመን። ከእኛም ይቅር በለን፤ ለእኛም ማረን፤ እዘንልንም። አንተ ረዳታችን ነህና፤ በካህዲዎች ህዝቦች ላይ እርዳን።» (ሱረቱል በቀራህ 2፡285-286) ማንም ሰው የሱረቱል በቀራህ የመጨረሻዎቹን ሁለት አያቶች በሌሊት የቀራ፣ እነዚያ ሁለት አያቶች በቂው ይሆኑለታል።
Reference: አል-ቡኻሪ፣ ፈትሁል ባሪ ፱/፺፬፣ ሙስሊም ፩/፭፻፶፬፣ ቁጥር ፰፻፯