Loading...
Language: Amharic
بِسْمِ اللَّـهِ الرَّحْمَـٰنِ الرَّحِيمِ قُلْ هُوَ اللَّـهُ أَحَدٌ ﴿١﴾ اللَّـهُ الصَّمَدُ ﴿٢﴾ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ ﴿٣﴾ وَلَمْ يَكُن لَّهُ كُفُوًا أَحَدٌ ﴿٤﴾
ቢስሚላሂር ረህማኒር ረሂም (1) ቁል ሁወላሁ አሀድ (2) አላሁስ-ሰመድ (3) ለም የሊድ ወ ለም ዩለድ (4) ወ ለም የኩን ለሁ ኩፉወን አሀድ
(1) በል እርሱ አላህ አንድ ነው። (2) አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው። (3) አልወለደም፣ አልተወለደምም። (4) ለእርሱም አንድም ቢጤ የለውም። (ሱረቱል ኢኽላስ 112፡ 1-4) ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) ለባልደረቦቻቸው፡- በሌሊት የቁርአንን አንድ ሶስተኛ መቅራት አትችሉምን? አሏቸው። ጉዳዩ ለእነሱ ከባድ ሆነባቸው። የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ከእኛ ውስጥ ያንን ማድረግ የሚችል ማነው? አሉ። ከዚያም እሳቸው እንዲህ አሉ፡- «ቁል ሁወላሁ አሀድ» ሱራ የቁርአን አንድ ሶስተኛ ነው።
Reference: ሰሂህ ሙስሊም፡ ፰፻፲፩