Loading...
Language: Amharic
ጃቢር (ረ.ዐ) እንዳሉት፣ የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) ሱረቱል ሰጅዳህ እና ሱረቱል ሙልክን ሳይቀሩ አይተኙም ነበር። [፩] አይሻ (ረ.ዐ) እንዳሉት፣ «የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) ሱረቱል በኒ ኢስራኢልን እና ሱረቱል ዙመርን ሳይቀሩ አይተኙም ነበር።» በሌላ ሀዲስ፣ አይሻ (ረ.ዐ) ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) ሱረቱል ሰጅዳህ እና ሱረቱል ዙመርን በየሌሊቱ ይቀሩ እንደነበር ተናግረዋል። [፪]
Reference: [፩] ሰሂህ (አልባኒ)። ቲርሚዚ፡ ፴፬፻፬ [፪] ሰሂህ (አልባኒ)። ቲርሚዚ፡ ፳፱፻፳