Loading...
Language: Amharic
اَللَّهُمَّ رَبَّ السَّمَوَاتِ السَّبْعِ وَرَبَّ الْأَرْضِ، وَرَبَّ الْعَرْشِ الْعَظِيمِ، رَبَّنَا وَرَبَّ كُلِّ شَيْءٍ، فَالِقَ الْحَبِّ وَالنَّوَى، وَمُنْزِلَ التَّوْرَاةِ وَالْإِنْجِيلِ، وَالْفُرْقَانِ، أَعُوْذُ بِكَ مِنْ شَرِّ كُلِّ شَيْءٍ أَنْتَ آخِذٌ بِنَاصِيَتِهِ، اَللَّهُمَّ أَنْتَ الْأَوَّلُ فَلَيْسَ قَبْلَكَ شَيْءٌ، وَأَنْتَ الْآخِرُ فَلَيسَ بَعْدَكَ شَيْءٌ، وَأَنْتَ الظَّاهِرُ فَلَيْسَ فَوْقَكَ شَيْءٌ، وَأَنْتَ الْبَاطِنُ فَلَيْسَ دُونَكَ شَيْءٌ، اقْضِ عَنَّا الدَّيْنَ وَأَغْنِنَا مِنَ الْفَقْرِ
አላሁመ ረበስ-ሰማዋቲስ-ሰብዒ ወ ረበል አርድ፣ ወ ረበል-አርሺል-አዚም፣ ረበና ወ ረበ ኩሊ ሸይኢን፣ ፋሊቀል-ሀቢ ወነዋ፣ ወ ሙንዚለት-ተውራቲ ወል-ኢንጂሊ፣ ወል-ፉርቃን፣ አዑዙ ቢከ ሚን ሸሪ ኩሊ ሸይኢን አንተ አኺዙን ቢናሲየቲህ። አላሁመ አንተል-አወሉ ፈለይሰ ቀብለከ ሸይኡን፣ ወ አንተል-አኺሩ ፈለይሰ በዕደከ ሸይኡን፣ ወ አንተዝ-ዛሂሩ ፈለይሰ ፈውቀከ ሸይኡን፣ ወ አንተል-ባጢኑ ፈለይሰ ዱነከ ሸይኡን፣ ኢቅዲ አነድ-ደይነ ወ አግኒና ሚነል-ፈቅር
አላህ ሆይ! የሰባቱ ሰማያት ጌታ፣ የምድር ጌታ፣ የትልቁ አርሽ ጌታ፣ ጌታችን እና የሁሉም ነገር ጌታ፣ ፍሬን እና የቴምር እምብርት ከፋይ (አብቃይ)፣ ተውራትን፣ ኢንጂልን እና ፉርቃንን (ቁርአንን) ያወረድክ። እኔ ከአንተ ዘንድ ግንባሩን ከያዝከው (ከምታዝዘው) ነገር ሁሉ ክፋት እጠበቃለሁ። አላህ ሆይ አንተ የመጀመሪያው ነህ ከአንተ በፊት ምንም ነገር የለም፣ አንተ የመጨረሻው ነህ ከአንተ በኋላ ምንም ነገር የለም። አንተ ግልጽ (ከፍ ያለ) ነህ ከአንተ በላይ ምንም ነገር የለም፣ አንተ ስውር (ቅርብ) ነህ ከአንተ በታች (የቀረበ) ምንም ነገር የለም። እዳችንን ክፈልልን፣ ከድህነት ግን አብቃቃን (ጠብቀን)። አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት፣ የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) ወደ አልጋችን በምንሄድበት ጊዜ ቃላቶቹን (ከላይ የተጠቀሱትን) እንድንናገር ያዙን ነበር። በሌላ ዘገባ፣ ፋጢማ (ረ.ዐ) ኻዲማን (አገልጋይን) በጠየቋቸው ጊዜ፣ እርሳቸው ዱዓውን አስተማሯት።
Reference: ሙስሊም፡ ፳፯፻፲፫፣ ሰሂህ (አልባኒ)። ቲርሚዚ፡ ፴፬፻፹፩