Loading...
Language: Amharic
بِاسْمِكَ رَبِّي وَضَعْتُ جَنْبِي، وَبِكَ أَرْفَعُهُ، فَإِنْ أَمْسَكْتَ نَفْسِي فَارْحَمْهَا، وَإِنْ أَرْسَلْتَهَا فَاحْفَظْهَا، بِمَا تَحْفَظُ بِهِ عِبَادَكَ الصَّالِحِينَ
ቢስሚከ ረቢ ወዳዕቱ ጀንቢ፣ ወ ቢከ አርፈኡሁ፣ ፈኢን አምሰክተ ነፍሲ ፈርሀምሀ፣ ወ ኢን አርሰልተሀ ፈህፈዝሀ፣ ቢማ ተህፈዙ ቢሂ ኢባደከስ-ሳሊሂን
ጌታዬ ሆይ በስምህ ጎኔን አሳረፍኩ (ተኛሁ)፣ በአንተም አነሳዋለሁ። ነፍሴን ከያዝካት (ከወሰድካት) እዘንላት፣ ከላክካትም (ከመለስካትም) መልካም ባሮችህን በምትጠብቅበት ነገር ጠብቃት። አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንደተረኩት፡ ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- «ከእናንተ አንዳችሁ ወደ አልጋ በሄደ ጊዜ፣ አልጋውን በወገብ ሽርጡ የውስጥ ክፍል ያራግፍ፣ ከእርሱ በኋላ ምን እንደመጣበት አያውቅምና። እና ከዚያ እንዲህ ይበል፡ (ዱዓው ከላይ ተጠቅሷል)»
Reference: አል-ቡኻሪ ፲፩/፻፳፮ ቁጥር ፷፫፻፳፣ ሙስሊም ፬/፳፻፹፬ ቁጥር ፳፯፻፲፬