Loading...
Language: Amharic
ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- «ወደ አልጋህ ለመሄድ ከፈለግህ፣ ውዱእ አድርግ፣ በቀኝ ጎንህ ተኛ እና ከዚያ እንዲህ ብለህ ለምን፡-
اَللَّهُمَّ أَسْلَمْتُ نَفْسِي إِلَيْكَ، وَفَوَّضْتُ أَمْرِي إِلَيْكَ، وَوَجَّهْتُ وَجْهِيْ إِلَيْكَ، وَأَلْجَأْتُ ظَهْرِي إِلَيْكَ، رَغْبَةً وَرَهْبَةً إِلَيْكَ، لَا مَلْجَأَ وَلَا مَنْجَا مِنْكَ إِلَّا إِلَيْكَ، آمَنْتُ بِكِتَابِكَ الَّذِي أَنْزَلْتَ، وَبِنَبِيِّكَ الَّذِي أَرْسَلْتَ
አላሁመ አስለምቱ ነፍሲ ኢለይከ፣ ወ ፈወድቱ አምሪ ኢለይከ፣ ወ ወጀህቱ ወጅሂ ኢለይከ፣ ወ አልጀዕቱ ዝህሪ ኢለይከ፣ ረግበተን ወ ረህበተን ኢለይከ፣ ላ መልጀአ ወላ መንጃ ሚንከ ኢላ ኢለይከ፣ አመንቱ ቢኪታቢከ-ለዚ አንዘልተ ወ ቢነቢዪከ-ለዚ አርሰልተ
አላህ ሆይ፣ ነፍሴን (ራሴን) ለአንተ ሰጠሁ፣ ጉዳዬንም ለአንተ አስረከብኩ፣ ፊቴንም ወደ አንተ አዞርኩ፣ ጀርባዬንም በአንተ ተጠጋሁ፣ በአንተ ተስፋ በማድረግ እና አንተን በመፍራት። ከአንተ (ከቅጣትህ) መሸሻም ሆነ መዳኛ ከአንተ ዘንድ እንጂ የለም። ባወረድከው መጽሐፍህ እና በላክከው ነቢይህ አምኛለሁ። ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) ይህንን ዱዓ ላስተማሩት ሰው እንዲህ አሉት፡- በዚያች ሌሊት ብትሞት፣ በፊጥራ (በኢስላም ተፈጥሮ) ላይ ትሞታለህ።
Reference: አል-ቡኻሪ፣ ፈትሁል ባሪ ፲፩/፻፲፫ ቁጥር ፷፫፻፲፫፣ ሙስሊም ፬/፳፻፹፩ ቁጥር ፳፯፻፲