Loading...
Language: Amharic
لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ وَحْدَهُ لَا شَرِيْكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ، وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيْرٌ، سُبْحَانَ اللَّهِ، وَالْحَمْدُ لِلَّهِ، وَلَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ، وَاللَّهُ أَكْبَرُ، وَلَا حَوْلَ وَلَا قُوَّةَ إِلَّا بِاللَّهِ الْعَلِيِّ الْعَظِيْمِ، رَبِّ اغْفِرْ لِي
ላ ኢላሀ ኢለላሁ ወህደሁ ላ ሸሪከ ለሁ፣ ለሁል-ሙልኩ ወ ለሁል-ሀምዱ፣ ወ ሁወ አላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር። ሱብሀነላሂ፣ ወልሀምዱ ሊላሂ፣ ወላ ኢላሀ ኢለላሁ، ወላሁ አክበር፣ ወላ ሀውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላሂል-አሊዪል-አዚም። ረቢግፊር ሊ
ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ (አምላክ) የለም፣ እሱ ብቸኛ ነው፣ ምንም አጋር የለውም፣ ንግስና የእርሱ ነው ምስጋናም ሁሉ ለእርሱ ነው፣ እርሱም በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው። ጥራት ለአላህ ይገባው፣ ምስጋናም ለአላህ ይገባው፣ ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም፣ አላህ ከሁሉ በላይ ታላቅ ነው፣ በአላህ እንጂ ምንም ብልሃትም ሆነ ኃይል የለም፣ እርሱ የሁሉም በላይ እና ታላቅ ነው። ጌታዬ ሆይ ማረኝ (ይቅር በለኝ)። ኡባዳህ ቢን አል-ሳሚት (ረ.ዐ) እንደዘገቡት የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- «ማንም ሰው ተኝቶ እያለ ደንግጦ (ነቅቶ) እነዚህን ካለ እና ከሰገደ፣ ጸሎቱ ምላሽ ያገኛል። ከተነሳ፣ ውዱእ ካደረገ፣ እና ከሰገደ፣ ሶላቱ ተቀባይነት ይኖረዋል።»
Reference: ሰሂህ (አልባኒ)። አቡ ዳውድ፡ ፶፻፷