Loading...
Language: Amharic
اَللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ الْجَنَّةَ وَأَعُوذُ بِكَ مِنَ النَّارِ
አላሁመ ኢኒ አስአሉከል-ጀነተ ወ አ'ኡዙ ቢከ ሚነን-ናር
አላህ ሆይ፣ ጀነትን እጠይቅሃለሁ፤ ከእሳትም በአንተ እጠበቃለሁ። አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንደተረኩት፡- የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) አንድን ሰው፣ «በሶላትህ ውስጥ ምን ብለህ ዱዓ ታደርጋለህ?» ብለው ጠየቁት። ሰውዬውም፣ ተሸሁድን አነባለሁ እናም - (ዱዓው ከላይ ተጠቅሷል) እላለሁ፤ እኔ እንደ እርሶ በሚያምር ሁኔታ፣ ወይም እንደ ሙዓዝ ዱዓ ማድረግ አልችልም! አላቸው። ከዚያም ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ)፣ «እኛም እንደ አንተ አይነት ዱዓ እናደርጋለን!» አሉት።
Reference: ሰሂህ (አልባኒ)። ኢብን ማጃህ፡ ፱፻፲