Loading...
Language: Amharic
መንቃት እና ውዱእ ማድረግ እና የሱረቱል አሊ-ዒምራንን የመጨረሻዎቹን አስር አንቀጾች መቅራት፡-
إِنَّ فِي خَلْقِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَاخْتِلَافِ اللَّيْلِ وَالنَّهَارِ لَآيَاتٍ لِّأُولِي الْأَلْبَابِ ﴿١٩٠﴾ الَّذِينَ يَذْكُرُونَ اللَّهَ قِيَامًا وَقُعُودًا وَعَلَىٰ جُنُوبِهِمْ وَيَتَفَكَّرُونَ فِي خَلْقِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ رَبَّنَا مَا خَلَقْتَ هَٰذَا بَاطِلًا سُبْحَانَكَ فَقِنَا عَذَابَ النَّارِ ﴿١٩١﴾ رَبَّنَا إِنَّكَ مَن تُدْخِلِ النَّارَ فَقَدْ أَخْزَيْتَهُ ۖ وَمَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ أَنصَارٍ ﴿١٩٢﴾ رَّبَّنَا إِنَّنَا سَمِعْنَا مُنَادِيًا يُنَادِي لِلْإِيمَانِ أَنْ آمِنُوا بِرَبِّكُمْ فَآمَنَّا ۚ رَبَّنَا فَاغْفِرْ لَنَا ذُنُوبَنَا وَكَفِّرْ عَنَّا سَيِّئَاتِنَا وَتَوَفَّنَا مَعَ الْأَبْرَارِ ﴿١٩٣﴾ رَبَّنَا وَآتِنَا مَا وَعَدتَّنَا عَلَىٰ رُسُلِكَ وَلَا تُخْزِنَا يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۗ إِنَّكَ لَا تُخْلِفُ الْمِيعَادَ ﴿١٩٤﴾ فَاسْتَجَابَ لَهُمْ رَبُّهُمْ أَنِّي لَا أُضِيعُ عَمَلَ عَامِلٍ مِّنكُم مِّن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ ۖ بَعْضُكُم مِّن بَعْضٍ ۖ فَالَّذِينَ هَاجَرُوا وَأُخْرِجُوا مِن دِيَارِهِمْ وَأُوذُوا فِي سَبِيلِي وَقَاتَلُوا وَقُتِلُوا لَأُكَفِّرَنَّ عَنْهُمْ سَيِّئَاتِهِمْ وَلَأُدْخِلَنَّهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ ثَوَابًا مِّنْ عِندِ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ عِندَهُ حُسْنُ الثَّوَابِ ﴿١٩٥﴾ لَا يَغُرَّنَّكَ تَقَلُّبُ الَّذِينَ كَفَرُوا فِي الْبِلَادِ ﴿١٩٦﴾ مَتَاعٌ قَلِيلٌ ثُمَّ مَأْوَاهُمْ جَهَنَّمُ ۚ وَبِئْسَ الْمِهَادُ ﴿١٩٧﴾ لَٰكِنِ الَّذِينَ اتَّقَوْا رَبَّهُمْ لَهُمْ جَنَّاتٌ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا نُزُلًا مِّنْ عِندِ اللَّهِ ۗ وَمَا عِندَ اللَّهِ خَيْرٌ لِّلْأَبْرَارِ ﴿١٩٨﴾ وَإِنَّ مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ لَمَن يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَمَا أُنزِلَ إِلَيْكُمْ وَمَا أُنزِلَ إِلَيْهِمْ خَاشِعِينَ لِلَّهِ لَا يَشْتَرُونَ بِآيَاتِ اللَّهِ ثَمَنًا قَلِيلًا ۗ أُولَٰئِكَ لَهُمْ أَجْرُهُمْ عِندَ رَبِّهِمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ سَرِيعُ الْحِسَابِ ﴿١٩٩﴾ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اصْبِرُوا وَصَابِرُوا وَرَابِطُوا وَاتَّقُوا اللَّهَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ ﴿٢٠٠﴾
ኢንነ ፊ ኸልቂስ ሰማዋቲ ወል አርዲ ወኽቲላፊል ለይሊ ወን ነሀሪ ለ አያቲል ሊኡሊል አልባብ። አለዚነ የዝኩሩነላሀ ቂያመን ወቁዑደን ወዐላ ጁኑቢሂም ወየተፈከሩነ ፊ ኸልቂስ ሰማዋቲ ወል አርዲ ረበና ማ ኸለቅተ ሀዛ ባጢለን ሱብሀነከ ፈቂና ዐዛበን ናር። ረበና ኢንነከ መን ቱድኺሊን ናረ ፈቀድ አኽዘይተሁ ወማ ሊዝዞሊሚነ ሚን አንሷር። ረበና ኢንነና ሰሚዕና ሙናዲየን ዩናዲ ሊል ኢማኒ አን አሚኑ ቢረቢኩም ፈአመና፤ ረበና ፈግፊር ለና ዙኑገና ወከፊር ዐንና ሰይይአቲና ወተወፈና መዐል አብራር። ረበና ወአቲና ማ ወዐድተና ዐላ ሩሱሊከ ወላ ቱኽዚና የውመል ቂያመህ፤ ኢንነከ ላ ቱኽሊፉል ሚዒአድ። ፈስተጃበ ለሁም ረቡሁም አንኒ ላ ኡዲዑ ዐመለ ዐሚሊም ሚንኩም ሚን ዘከሪን አው ኡንሳ፤ ባዕዱኩም ሚን ባዕድ፤ፈለዚነ ሀጀሩ ወኡኽሪጁ ሚን ዲያሪሂም ወኡዙ ፊ ሰቢሊ ወቃተሉ ወቁቲሉ ላኡከፊረንነ ዐንሁም ሰይይአቲሂም ወላኡድኺለነሁም ጅናቲን ተጅሪ ሚን ተህቲሀል አንሀር፤ ሰዋበን ሚን ዒንዲላህ፤ ወላሁ ዒንደሁ ሁስኑስ ሰዋብ። ላ የጉረነከ ተቀሉቡለዚነ ከፈሩ ፊል ቢላድ። መታዑን ቀሊሉን ሱምመ መእዋሁም ጀሀነሙ ወቢእሰል ሚሀድ። ላኪኒለዚነ ተቀው ረበሁም ለሁም ጀናቱ ተጅሪ ሚን ተህቲሀል አንሀሩ ኻሊዲነ ፊሀ ኑዙለን ሚን ዒንዲላህ፤ ወማ ዒንደላሂ ኸይሩል ሊል አብራር። ወኢንነ ሚን አህሊል ኪታቢ ለመን ዩእሚኑ ቢላሂ ወማ ኡንዚለ ኢለይኩም ወማ ኡንዚለ ኢለይሂም ኻሺዒነ ሊላሂ ላ የሽተሩነ ቢአያቲላሂ ሰመነን ቀሊላ፤ ኡላኢከ ለሁም አጅሩሁም ዒንደ ረቢሂም፤ ኢንነላሀ ሰሪዑል ሂሳብ። ያ አዩሀለዚነ አመኑስ ቢሩ ወሷቢሩ ወራቢጡ ወተቁላሀ ለዐለኩም ቱፍሊሁን።
(190) በሰማያትና በምድር መፍጠር፣ በሌሊትና በቀንም መተካካት፣ ለልቦና ባለቤቶች ምልክቶች አሉበት። (191) ለነዚያ ቆመው፣ ተቀምጠውም፣ በጎኖቻቸውም ተኝተው አላህን ለሚያወሱ፣ በሰማያትና በምድር አፈጣጠርም ለሚያስተነትኑ፣ «ጌታችን ሆይ! ይህንን በከንቱ አልፈጠርከውም፤ ጥራት ይገባህ፤ ከእሳት ቅጣትም ጠብቀን» ለሚሉ (ምልክቶች አሉበት)። (192) «ጌታችን ሆይ! አንተ እሳትን የምታስገባውን ሰው፣ በእርግጥ አዋረድከው፤ ለበደለኞችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም።» (193) «ጌታችን ሆይ! እኛ “በጌታችሁ እመኑ” ሲል ወደ እምነት የሚጠራን ጠሪ፣ ሰማን፤ አመንንም። ጌታችን ሆይ! ኃጢአቶቻችንን ማርልን፤ ክፉ ስራዎቻችንንም ከእኛ አብስልን (ሰርዝልን)፤ ከደጋጎቹም ጋር ግደለን።» (194) «ጌታችን ሆይ! በመልክተኞችህም ላይ የቀጠርከንን ስጠን፤ በትንሳኤ ቀንም አታዋርደን፤ አንተ ቃል ኪዳንን አታፈርስምና።» (195) ጌታቸውም ለነሱ (እንዲህ ሲል) ለመነላቸው፡- «እኔ ከእናንተ ከወንድ ወይም ከሴት የሰራን ሰራተኛ ስራ አልያጠፋም፤ ከፊላችሁ ከከፊሉ ነው። እነዚያ የተሰደዱትም፣ ከቤቶቻቸውም የተወጡትም፣ በመንገዴም የተሰቃዩትም፣ የተጋደሉትም፣ የተገደሉትም፣ ከእነሱ ኃጢአቶቻቸውን በእርግጥ አብሳለሁ (እሰርዛለሁ)፤ ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውንም ገነቶች በእርግጥ አስገባቸዋለሁ። ከአላህ ዘንድ ዋጋ ይሆን ዘንድ (ይህንን እሰጣቸዋለሁ)። መልካም ዋጋም ያለው እርሱ አላህ ዘንድ ነው።» (196) የነዚያ የካዱት ሰዎች በየሀገሩ (ለመነገድ) መዘዋወር አያታላይህ። (197) (ይህ) ጥቂት መጠቀሚያ ናት፤ ከዚያም መኖሪያቸው ገሀነም ናት፤ ምን ትክፉ ምንጣፍ! (198) ግን እነዚያ ጌታቸውን የፈሩ፣ ለነሱ ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች በውስጧ ዘውታሪዎች ሲሆኑ አላቸው፤ ከአላህ ዘንድ የሆነ መስተንግዶ (አላቸው)። አላህ ዘንድ ያለውም ነገር ለደጋጎቹ በላጭ ነው። (199) ከመጽሐፉም ሰዎች (ከአይሁድና ክርስቲያን) ለአላህ የሚዋረዱ ሆነው በአላህና ወደ እናንተ በተወረደው፣ ወደ እነርሱም በተወረደው የሚያምኑ፣ በአላህ አንቀጾች ጥቂትን ዋጋ የማይገዙ አልሉ። እነዚያ ለእነሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው፤ አላህ ምርመራው ፈጣን ነውና። (200) እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ታገሱ፣ ተበራቱም፣ (በጂሃድ) ተሰለፉም፣ ትድኑም ዘንድ አላህን ፍሩ። (ሱረቱል አሊ-ዒምራን 3፡ 190-200) ከዚያም ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) ተነሱ እና ሁለት ረከዓዎችን ሰገዱ፤ በዚያ ሶላት ውስጥ ቂያምን፣ ሩኩዕን እና ሱጁድን አረዘሙ። ሶላቱን ከጨረሱ በኋላ እንቅልፍ ወሰዳቸው ....
Reference: አል-ቡኻሪ፣ አል-አስቀላኒ እንዳሉት፣ ፈትሁል-ባሪ ፰/፪፻፭፯ ቁጥር ፵፭፻፷፱፤ ሙስሊም ፩/፭፻፴ ቁጥር ፪፻፶፮