Loading...
Language: Amharic
اِلْبَسْ جَدِيدًا وَعِشْ حَمِيدًا وَمُتْ شَهِيدًا
ኢልበስ ጀዲደን፣ ወ ዒሽ ሀሚደን፣ ወ ሙት ሸሂደን
አዲስን ልበስ፣ የተመሰገንክ (ክቡር) ሆነህ ኑር፣ እና ሰማዕት (ሸሂድ) ሆነህ ሙት። ኢብን ኡመር (ረ.ዐ) እንደተረኩት፡ ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) በኡመር ላይ ነጭ ልብስ አዩ እና እንዲህ አሉ፡- «ይህ ልብስህ አዲስ ነው ወይስ የታጠበ ይመስላል?» እርሱም አለ፡- «ይልቁንም አዲስ ነው።» ከዚያም ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) አሉ- (ዱዓው ከላይ ተጠቅሷል)። ኡመር (ረ.ዐ) አሉ፡- «የአላህ መልእክተኛ ሆይ! እኔም ለአንተ የምጸልየው ያንኑ ነው።»
Reference: ሰሂህ (አልባኒ)። ኢብን ማጃህ፡ ፴፭፻፶፰