Loading...
Language: Amharic
ዑመር ኢብን አል-ኸጣብ (ረ.ዐ) እንደተረኩት፣ የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡ ሙአዚኑ «አላሁ አክበር አላሁ አክበር» ሲል፣ ከእናንተ መካከል አንዱ «አላሁ አክበር አላሁ አክበር» ካለ፤ ሙአዚኑ «አሽሀዱ አን ላኢላሀ ኢለላህ» ሲል፣ እርሱ «አሽሀዱ አን ላኢላሀ ኢለላህ» ካለ፤ ሙአዚኑ «አሽሀዱ አነ ሙሀመደር ረሱሉላህ» ሲል፣ እርሱ «አሽሀዱ አነ ሙሀመደር ረሱሉላህ» ካለ፤ ሙአዚኑ «ሀያ አለስ ሶላህ» ሲል፣ እርሱ «ላ ሀውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ» ካለ፤ ሙአዚኑ «ሀያ አለል ፈላህ» ሲል፣ እርሱ «ላ ሀውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ» ካለ፤ ሙአዚኑ «አላሁ አክበር አላሁ አክበር» ሲል፣ እርሱ «አላሁ አክበር አላሁ አክበር» ካለ፣ ከዚያም ሙአዚኑ «ላ ኢላሀ ኢለላህ» ሲል፣ እርሱ «ላ ኢላሀ ኢለላህ» ካለ እነዚህን ነገሮች ከልቡ ከተናገረ ጀነት ይገባል።
Reference: ሙስሊም፡ ፫፻፹፭