Loading...
Language: Amharic
ሻህር ቢን ሀውሸብ (ረ.ዐ) እንዲህ አሉ፡- «ለኡሙ ሰለማ (ረ.ዐ)፡- ‘የአማኞች እናት ሆይ! የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) ከእርሶ ዘንድ በነበሩበት ጊዜ አብዛኛውን ጊዜ የሚያደርጉት ዱዓ ምን ነበር?’ አልኳቸው። እሳቸውም፡- ‘አብዛኛውን ጊዜ የሚያደርጉት ዱዓ -
يَا مُقَلِّبَ الْقُلُوبِ ثَبِّتْ قَلْبِيْ عَلَى دِيْنِكَ
ያ ሙቀሊበል-ቁሉቢ፣ ሰቢት ቀልቢ 'አላ ዲኒክ
አንተ ልቦችን የምታገላብጥ (የምታዞር) ሆይ! ልቤን በዲንህ (በሃይማኖትህ) ላይ አጽናልኝ። የሚል ነበር’ አሉ። ከዚያም እኔ፡- የአላህ መልእክተኛ ሆይ (ሶ.ዐ.ወ)፣ ለምን ይህንን ዱዓ አብዝተው ያደርጋሉ? አልኳቸው። እሳቸውም እንዲህ አሉ፡- ‘ኡሙ ሰለማ ሆይ! በእርግጥ የትኛውም የሰው ልጅ ልቡ በአላህ ጣቶች መካከል ባሉ ሁለት ጣቶች መሃል ነውና፤ የፈለገውን ያጸናዋል፣ የፈለገውን ደግሞ ያጠመዋል (ያሳስተዋል)’።
Reference: ሰሂህ (አልባኒ)። ቲርሚዚ፡ ፴፭፻፳፪