Loading...
Language: Amharic
ውዱን በደንብ ካደረጉ በኋላ፣ አንድ ሰው እንዲህ ማለት አለበት፡-
أَشْهَدُ أَنْ لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ وَحْدَهُ لَا شَرِيْكَ لَهُ وَأَشْهَدُ أَنَّ مُحَمَّدًا عَبْدُهُ وَرَسُوْلُهُ
አሽ-ሀዱ አን ላ ኢላሀ ኢለላሁ ወህደሁ ላ ሸሪከ ለሁ ወ አሽ-ሀዱ አነ ሙሀመደን አብዱሁ ወ ረሱሉሁ
ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ ብቻውን፣ ምንም አጋር እንደሌለው እመሰክራለሁ፤ እና ሙሐመድ አገልጋዩ እና መልእክተኛው (ሶ.ዐ.ወ) መሆናቸውን እመሰክራለሁ። ኡቅባ ቢን አሚር (ረ.ዐ) እንደዘገቡት፡ የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ፡ ማንኛውም ሙስሊም ውዱን በደንብ ካደረገ፣ ከዚያም ቆሞ ሁለት ረከዓዎችን ከሰገደ ልቡን እንዲሁም ፊቱን ወደ እነርሱ ካደረገ፣ ጀነት ለእርሱ የተረጋገጠች ትሆናለች።
Reference: ሙስሊም፡ ፪፻፴፬ ፣ ፭፻፸፮