Loading...
Language: Amharic
ኢብን አባስ (ረ.ዐ) እንዳሉት፡ ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) ተሀጁድን ለመስገድ በሌሊት ሲቆሙ፣ ይህንን ይቅሩ ነበር፡
اَللَّهُمَّ لَكَ الْحَمْدُ أَنْتَ قَيِّمُ السَّمَوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَنْ فِيهِنَّ وَلَكَ الْحَمْدُ، لَكَ مُلْكُ السَّمَوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَنْ فِيهِنَّ، وَلَكَ الْحَمْدُ أَنْتَ نُورُ السَّمَوَاتِ وَالْأَرْضِ، وَلَكَ الْحَمْدُ أَنْتَ الْحَقُّ، وَوَعْدُكَ الْحَقُّ، وَلِقَاؤُكَ حَقٌّ، وَقَوْلُكَ حَقٌّ، وَالْجَنَّةُ حَقٌّ، وَالنَّارُ حَقٌّ، وَالنَّبِيُّونَ حَقٌّ، وَمُحَمَّدٌ ﷺ حَقٌّ، وَالسَّاعَةُ حَقٌّ، اَللَّهُمَّ لَكَ أَسْلَمْتُ، وَبِكَ آمَنْتُ وَعَلَيْكَ تَوَكَّلْتُ، وَإِلَيْكَ أَنَبْتُ، وَبِكَ خَاصَمْتُ، وَإِلَيْكَ حَاكَمْتُ، فَاغْفِرْ لِي مَا قَدَّمْتُ وَمَا أَخَّرْتُ، وَمَا أَسْرَرْتُ وَمَا أَعْلَنْتُ، أَنْتَ الْمُقَدِّمُ وَأَنْتَ الْمُؤَخِّرُ، لَا إِلَهَ إِلَّا أَنْتَ (لَا إِلَهَ غَيْرُكَ)
አላሁመ ለከል-ሀምዱ። አንተ ቀይይሙስ-ሰማዋቲ ወል-አርዲ ወ መን ፊሂነ። ወለከል-ሀምዱ፣ ለከ ሙልኩስ-ሰማዋቲ ወል-አርዲ ወ መን ፊሂነ። ወለከል-ሀምዱ፣ አንተ ኑሩስ-ሰማዋቲ ወል-አርዲ። ወለከል-ሀምዱ፣ አንተል-ሀቁ ወ ወዕዱከል-ሀቁ፣ ወ ሊቃኡከ ሀቁን፣ ወ ቀውሉከ ሀቁን፣ ወል-ጀነቱ ሀቁን ወን-ናሩ ሀቁን ወነቢዩነ ሀቁን። ወ ሙሀመዱን (ሶ.ዐ.ወ) ሀቁን፣ ወስ-ሰዓቱ ሀቁን። አላሁመ ለከ አስለምቱ ወቢከ አመንቱ፣ ወ አለይከ ተወከልቱ፣ ወ ኢለይከ አነብቱ ወ ቢከ ኻሰምቱ፣ ወ ኢለይከ ሓከምቱ ፈግፊር ሊ ማ ቀደምቱ ወማ አኽ-ኸርቱ ወማ አስ-ረርቱ ወማ አዕለንቱ፣ አንተል-ሙቀዲሙ ወ አንተል ሙአኽ-ኺሩ፣ ላ ኢላሀ ኢላ አንተ
አላህ ሆይ! ምስጋና ሁሉ ለአንተ ነው፣ የሰማያት እና የምድር እና በውስጣቸው ያለው ሁሉ ጠባቂ አንተ ነህ። ምስጋና ሁሉ ለአንተ ነው፤ የሰማያት እና የምድር እና በውስጣቸው ያለው ሁሉ ንግስና ያንተ ነው። ምስጋና ሁሉ ለአንተ ነው፤ የሰማያት እና የምድር ብርሃን አንተ ነህ። እና ምስጋና ሁሉ ለአንተ ነው፤ የሰማያት እና የምድር ንጉስ አንተ ነህ፤ እና ምስጋና ሁሉ ለአንተ ነው፤ አንተ እውነት ነህ እና ቃልህ እውነት ነው፣ እና አንተን መገናኘት እውነት ነው፣ ቃልህ እውነት ነው እና ጀነት እውነት ናት እና ገሃነም እውነት ናት እና ሁሉም ነቢያት (ሰላም በእነሱ ላይ ይሁን) እውነት ናቸው፤ እና ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) እውነት ነው፣ እና የትንሳኤ ቀን እውነት ነው። አላህ ሆይ! እኔ (ፈቃዴን) ለአንተ ሰጠሁ፤ በአንተ አመንኩ እና በአንተ ተመካሁ። እና ወደ አንተ ተመለስኩ፣ እና በእርዳታህ ተከራከርኩ (ከተቃዋሚዎቼ፣ ካሀዲዎች ጋር) እና አንተን ዳኛ አደረግኩ (በእኛ መካከል እንድትፈርድ)። ስለዚህ ያለፈውን እና ወደፊት የሚመጡትን ኃጢአቶቼን ማርልኝ፤ እና የደበቅኩትን ወይም የገለጽኩትን እና (አንዳንድ ሰዎችን) ወደ ፊት የምታደርግ እና (አንዳንዶችን) ወደ ኋላ የምታደርግ አንተ ነህ። ከአንተ በስተቀር የሚመለክ የለም።
Reference: ቡኻሪ፡ ፲፩፻፳