Loading...
Language: Amharic
በአቡ በክር አስ-ሲዲቅ (ረ.ዐ) እንደተረካው፡ የአላህ መልእክተኛን (ሶ.ዐ.ወ) በጸሎቴ አላህን እንድለምንበት የሆነን ዱዓ እንዲያስተምሩኝ ጠየቅኩ። እሳቸውም እንዲህ እንድል ነገሩኝ፡
اَللَّهُمَّ إِنِّي ظَلَمْتُ نَفْسِيْ ظُلْمًا كَثِيْرًا وَلَا يَغْفِرُ الذُّنُوبَ إِلَّا أَنْتَ فَاغْفِرْ لِي مَغْفِرَةً مِنْ عِنْدِكَ وَارْحَمْنِيْ إِنَّكَ أَنْتَ الْغَفُوْرُ الرَّحِيْمُ
አላሁመ ኢኒ ዘለምቱ ነፍሲ ዙልመን ከሲረን፣ ወ ላ የርግፊሩዝ-ዙኑበ ኢላ አንተ፣ ፈግፊር ሊ መግፊረተን ሚን ኢንዲከ ወርሀምኒ ኢነከ አንተል-ገፉሩር-ረሂም
አላህ ሆይ፣ እኔ ነፍሴን በብዙ በደል በድያለሁ እና ከአንተ በስተቀር ኃጢአቶችን የሚምር የለም። ስለዚህ፣ ከአንተ ዘንድ የሆነን ምህረት ለግሰኝ እና እዘንልኝ። በርግጥ አንተ መዳሪ፣ አዛኝ ነህ።
Reference: ቡኻሪ፡ ፰፻፴፬