Loading...
Language: Amharic
አብደላህ ኢብን ዑመር (ረ.ዐ) እንደዘገቡት፡ ከአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) ጋር እየሰገድን ሳለ፣ ከሰዎቹ አንዱ እንዲህ አለ፡
اَللَّهُ أَكْبَرُ كَبِيْرًا، وَالْحَمْدُ لِلَّهِ كَثِيرًا، وَسُبْحَانَ اللَّهِ بُكْرَةً وَأَصِيلًا
አላሁ አክበር ከቢረን፣ ወልሀምዱ ሊላሂ ከሲረን፣ ወ ሱብሀነላሂ ቡክረተን ወ አሲለ
አላህ ከሁሉ ታላቅ ነው፣ በጣም ታላቅ። ምስጋና ለአላህ ይሁን፣ በብዛት። ክብር ለአላህ ይሁን፣ በቀኑ መጀመሪያ (ጠዋት) እና መጨረሻ (ምሽት) ላይ። የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) አሉ፡ እንደዚህ እና እንደዚህ ያለ ቃል የተናገረው ማን ነው? ከሰዎቹ መካከል አንድ ሰው (እነዚህን ቃላት የቀራ) አለ፡ እኔ! ያ የአላህ መልእክተኛ ሆይ!። እሳቸውም (ሶ.ዐ.ወ) አሉ፡ አባባሉ አስገረመኝ ምክንያቱም ለዚህ ዱዓ፣ የሰማይ በሮች ተከፍተዋልና። ኢብን ዑመር (ረ.ዐ) አሉ፡ የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) ይህንን ሲሉ ከሰማሁ በኋላ እነሱን (ይህንን ዱዓ መቅራት) አልተውኩም።
Reference: ሙስሊም፡ ፮፻፩