Loading...
Language: Amharic
የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- «ለአላህ በጣም ተወዳጅ የሆኑ አባባሎች አራት ናቸው። ከእነርሱ በየትኛውም ቢጀመር (አላህን በማውሳት እስከሆነ ድረስ) በአንተ ላይ ችግር የለውም። እነርሱም -
سُبْحَانَ اللَّهِ، وَالْحَمْدُ لِلَّهِ، وَلَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ، وَاللَّهُ أَكْبَرُ
ሱብሀነላሂ፣ ወልሀምዱ ሊላሂ፣ ወ ላ ኢላሀ ኢለላሁ፣ ወ አላሁ አክበር
አላህ ጥራት ይገባው፤ ምስጋና ሁሉ ለአላህ ነው፤ ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ እና አላህ ታላቅ ነው። [፩] የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- «(እነዚህን ቃላት) መናገሬ ፀሀይ በምትወጣበት ነገር ሁሉ ላይ (ከዚች ዓለም ንብረት ሁሉ) ለእኔ የበለጠ ተወዳጅ ነው።» [፪]
Reference: [፩] ሙስሊም፡ ፳፩፻፴፯ [፪] ሙስሊም፡ ፳፮፻፺፭