Loading...
Language: Amharic
የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) በዊትር ጸሎት ውስጥ ሶስት ሱራዎችን ይቀሩ ነበር፡ ሱረቱ አል-አእላ፡
بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ سَبِّحِ اسْمَ رَبِّكَ الْأَعْلَى ﴿١﴾ الَّذِي خَلَقَ فَسَوَّىٰ ﴿٢﴾ وَالَّذِي قَدَّرَ فَهَدَىٰ ﴿٣﴾ وَالَّذِي أَخْرَجَ الْمَرْعَىٰ ﴿٤﴾ فَجَعَلَهُ غُثَاءً أَحْوَىٰ ﴿٥﴾ سَنُقْرِئُكَ فَلَا تَنسَىٰ ﴿٦﴾ إِلَّا مَا شَاءَ اللَّهُ ۚ إِنَّهُ يَعْلَمُ الْجَهْرَ وَمَا يَخْفَىٰ ﴿٧﴾ وَنُيَسِّرُكَ لِلْيُسْرَىٰ ﴿٨﴾ فَذَكِّرْ إِن نَّفَعَتِ الذِّكْرَىٰ ﴿٩﴾ سَيَذَّكَّرُ مَن يَخْشَىٰ ﴿١٠﴾ وَيَتَجَنَّبُهَا الْأَشْقَى ﴿١١﴾ الَّذِي يَصْلَى النَّارَ الْكُبْرَىٰ ﴿١٢﴾ ثُمَّ لَا يَمُوتُ فِيهَا وَلَا يَحْيَىٰ ﴿١٣﴾ قَدْ أَفْلَحَ مَن تَزَكَّىٰ ﴿١٤﴾ وَذَكَرَ اسْمَ رَبِّهِ فَصَلَّىٰ ﴿١٥﴾ بَلْ تُؤْثِرُونَ الْحَيَاةَ الدُّنْيَا ﴿١٦﴾ وَالْآخِرَةُ خَيْرٌ وَأَبْقَىٰ ﴿١٧﴾ إِنَّ هَٰذَا لَفِي الصُّحُفِ الْأُولَىٰ ﴿١٨﴾ صُحُفِ إِبْرَاهِيمَ وَمُوسَىٰ ﴿١٩﴾
ቢስሚላሂር-ራህማኒር-ራሂም። (1) ቁል ሁወላሁ አሀድ። (2) አላሁስ-ሰመድ። (3) ለም የሊድ ወ ለም ዩለድ። (4) ወ ለም የኩን ለሁ ኩፉወን አሀድ
(1) የጌታህን፣ የዚያን የልዑሉን ስም አጥራ። (2) የዚያን (ፍጥረትን) የፈጠረውንና ያስተካከለውን። (3) የዚያንም (መኖሪያቸውን) የወሰነውንና የመራውን። (4) የዚያንም ግጦሽን ያወጣውን። (5) ጥቁር በስባሽም ያደረገውን። (6) (ቁርኣንን) በእርግጥ እናነብልሃለን፤ አትረሳውምም። (7) አላህ የሻው ሲቀር፤ እርሱ ግልጹንም፣ የሚደበቀውንም ያውቃልና። (8) ለቀላሊቱም (ሸሪዓ) እንገጥምሃለን። (9) ማስታወስ ከጠቀመ አስታውስ። (10) አላህን የሚፈራ ሰው ይገሰጻል። (11) ያም ክፉው ሰው ይርቃታል። (12) ያ ትልቁን እሳት የሚገባው። (13) ከዚያም በውስጧ የማይሞት የማይኖርም የሆነው። (14) ያ የተጥራራ ሰው በእርግጥ ዳነ። (15) የጌታውንም ስም ያወሳና የሰገደ። (16) ይልቁንም ቅርቢቱን ሕይወት ትመርጣላችሁ። (17) የመጨረሻይቱ (ዓለም) በላጭና ሁሌ ቀሪ ናት። (18) ይህ በመጀመሪያዎቹ ጽሑፎች ውስጥ አልለ። (19) በኢብራሂምና በሙሳ ጽሑፎች ውስጥ። (ሱረቱ አል-አእላ 87፡ 1-19) (ሱረቱ አል-ኢኽላስ) በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው። (1) በል፤ እርሱ አላህ አንድ ነው። (2) አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው። (3) አልወለደም አልተወለደምም። (4) ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
Reference: ሰሂህ (አልባኒ)። አቡ ዳውድ፡ ፲፬፻፳፫