Loading...
Language: Amharic
ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) ከእንቅልፋቸው በመነሳት የሱረቱ ሀል ኢምራንን የመጨረሻ ሩኩእ ይቀሩ ነበር። [1]
إِنَّ فِي خَلْقِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَاخْتِلَافِ اللَّيْلِ وَالنَّهَارِ لَآيَاتٍ لِّأُولِي الْأَلْبَابِ ﴿١٩٠﴾ الَّذِينَ يَذْكُرُونَ اللَّـهَ قِيَامًا وَقُعُودًا وَعَلَىٰ جُنُوبِهِمْ وَيَتَفَكَّرُونَ فِي خَلْقِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ رَبَّنَا مَا خَلَقْتَ هَـٰذَا بَاطِلًا سُبْحَانَكَ فَقِنَا عَذَابَ النَّارِ ﴿١٩١﴾ رَبَّنَا إِنَّكَ مَن تُدْخِلِ النَّارَ فَقَدْ أَخْزَيْتَهُ ۖ وَمَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ أَنصَارٍ ﴿١٩٢﴾ رَّبَّنَا إِنَّنَا سَمِعْنَا مُنَادِيًا يُنَادِي لِلْإِيمَانِ أَنْ آمِنُوا بِرَبِّكُمْ فَآمَنَّا ۚ رَبَّنَا فَاغْفِرْ لَنَا ذُنُوبَنَا وَكَفِّرْ عَنَّا سَيِّئَاتِنَا وَتَوَفَّنَا مَعَ الْأَبْرَارِ ﴿١٩٣﴾ رَبَّنَا وَآتِنَا مَا وَعَدتَّنَا عَلَىٰ رُسُلِكَ وَلَا تُخْزِنَا يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۗ إِنَّكَ لَا تُخْلِفُ الْمِيعَادَ ﴿١٩٤﴾فَاسْتَجَابَ لَهُمْ رَبُّهُمْ أَنِّي لَا أُضِيعُ عَمَلَ عَامِلٍ مِّنكُم مِّن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ ۖ بَعْضُكُم مِّن بَعْضٍ ۖ فَالَّذِينَ هَاجَرُوا وَأُخْرِجُوا مِن دِيَارِهِمْ وَأُوذُوا فِي سَبِيلِي وَقَاتَلُوا وَقُتِلُوا لَأُكَفِّرَنَّ عَنْهُمْ سَيِّئَاتِهِمْ وَلَأُدْخِلَنَّهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ ثَوَابًا مِّنْ عِندِ اللَّـهِ ۗ وَاللَّـهُ عِندَهُ حُسْنُ الثَّوَابِ ﴿١٩٥﴾ لَا يَغُرَّنَّكَ تَقَلُّبُ الَّذِينَ كَفَرُوا فِي الْبِلَادِ ﴿١٩٦﴾ مَتَاعٌ قَلِيلٌ ثُمَّ مَأْوَاهُمْ جَهَنَّمُ ۚ وَبِئْسَ الْمِهَادُ ﴿١٩٧﴾ لَـٰكِنِ الَّذِينَ اتَّقَوْا رَبَّهُمْ لَهُمْ جَنَّاتٌ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا نُزُلًا مِّنْ عِندِ اللَّـهِ ۗ وَمَا عِندَ اللَّـهِ خَيْرٌ لِّلْأَبْرَارِ ﴿١٩٨﴾ وَإِنَّ مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ لَمَن يُؤْمِنُ بِاللَّـهِ وَمَا أُنزِلَ إِلَيْكُمْ وَمَا أُنزِلَ إِلَيْهِمْ خَاشِعِينَ لِلَّـهِ لَا يَشْتَرُونَ بِآيَاتِ اللَّـهِ ثَمَنًا قَلِيلًا ۗ أُولَـٰئِكَ لَهُمْ أَجْرُهُمْ عِندَ رَبِّهِمْ ۗ إِنَّ اللَّـهَ سَرِيعُ الْحِسَابِ ﴿١٩٩﴾ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اصْبِرُوا وَصَابِرُوا وَرَابِطُوا وَاتَّقُوا اللَّـهَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ ﴿٢٠٠﴾
ኢንነ ፊ ኸልቂስ ሰማዋቲ ወል አርዲ ወኽቲላፊል ለይሊ ወን ነሀሪ ለ አያቲል ሊኡሊል አልባብ። አለዚነ የዝኩሩነላሀ ቂያመን ወቁዑደን ወዐላ ጁኑቢሂም ወየተፈከሩነ ፊ ኸልቂስ ሰማዋቲ ወል አርዲ ረበና ማ ኸለቅተ ሀዛ ባጢለን ሱብሀነከ ፈቂና ዐዛበን ናር። ረበና ኢንነከ መን ቱድኺሊን ናረ ፈቀድ አኽዘይተሁ ወማ ሊዝዞሊሚነ ሚን አንሷር። ረበና ኢንነና ሰሚዕና ሙናዲየን ዩናዲ ሊል ኢማኒ አን አሚኑ ቢረቢኩም ፈአመና፤ ረበና ፈግፊር ለና ዙኑገና ወከፊር ዐንና ሰይይአቲና ወተወፈና መዐል አብራር። ረበና ወአቲና ማ ወዐድተና ዐላ ሩሱሊከ ወላ ቱኽዚና የውመል ቂያመህ፤ ኢንነከ ላ ቱኽሊፉል ሚዒአድ። ፈስተጃበ ለሁም ረቡሁም አንኒ ላ ኡዲዑ ዐመለ ዐሚሊም ሚንኩም ሚን ዘከሪን አው ኡንሳ፤ ባዕዱኩም ሚን ባዕድ፤ፈለዚነ ሀጀሩ ወኡኽሪጁ ሚን ዲያሪሂም ወኡዙ ፊ ሰቢሊ ወቃተሉ ወቁቲሉ ላኡከፊረንነ ዐንሁም ሰይይአቲሂም ወላኡድኺለነሁም ጅናቲን ተጅሪ ሚን ተህቲሀል አንሀር፤ ሰዋበን ሚን ዒንዲላህ፤ ወላሁ ዒንደሁ ሁስኑስ ሰዋብ። ላ የጉረነከ ተቀሉቡለዚነ ከፈሩ ፊል ቢላድ። መታዑን ቀሊሉን ሱምመ መእዋሁም ጀሀነሙ ወቢእሰል ሚሀድ። ላኪኒለዚነ ተቀው ረበሁም ለሁም ጀናቱ ተጅሪ ሚን ተህቲሀል አንሀሩ ኻሊዲነ ፊሀ ኑዙለን ሚን ዒንዲላህ፤ ወማ ዒንደላሂ ኸይሩል ሊል አብራር። ወኢንነ ሚን አህሊል ኪታቢ ለመን ዩእሚኑ ቢላሂ ወማ ኡንዚለ ኢለይኩም ወማ ኡንዚለ ኢለይሂም ኻሺዒነ ሊላሂ ላ የሽተሩነ ቢአያቲላሂ ሰመነን ቀሊላ፤ ኡላኢከ ለሁም አጅሩሁም ዒንደ ረቢሂም፤ ኢንነላሀ ሰሪዑል ሂሳብ። ያ አዩሀለዚነ አመኑስ ቢሩ ወሷቢሩ ወራቢጡ ወተቁላሀ ለዐለኩም ቱፍሊሁን።
(190) በሰማያትና በምድር አፈጣጠር፣ በሌሊትና በቀንም መፈራረቅ፣ የአእምሮ ባለቤቶች ምልክቶች ናቸው። (191) እነዚያ ቆመውም፣ ተቀምጠውም፣ በጎኖቻቸውም ተኝተው አላህን የሚያወሱ፣ በሰማያትና በምድር አፈጣጠርም የሚያስተውሉ፣ «ጌታችን ሆይ! ይህንን በከንቱ አልፈጠርከውም፤ ጥራት ይገባህ፤ ከእሳትም ቅጣት ጠብቀን» የሚሉ ናቸው። (192) «ጌታችን ሆይ! አንተ እሳትን የምታስገባው ሰው በእርግጥ አዋረድከው፤ ለበደለኞችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም።» (193) «ጌታችን ሆይ! እኛ ወደ እምነት ጥሪን፣ በጌታችሁ እመኑ፣ በማለት የሚጠራን ጠሪ ሰማን፤ እናም አመንን፤ ጌታችን ሆይ! ኃጢአቶቻችንን ማርልን፤ ክፉ ሥራዎቻችንንም ከእኛ አብስልን፤ ከደጋጎቹም ሰዎች ጋር ግደለን።» (194) «ጌታችን ሆይ! በመልክተኞችህም ልሳን የቀጠርከንን ስጠን፤ በትንሣኤ ቀንም አታዋርደን፤ አንተ ቃል ኪዳንን አታፈርስምና።» (195) ጌታቸውም ለእነሱ፡- «እኔ ከእናንተ ከወንድ ወይም ከሴት የሠራን ሰው ሥራ አልያጠፋም፤ ከፊላችሁ ከከፊሉ ነውና፤ እነዚያ የተሰደዱትም፣ ከአገራቸውም የተወጡት፣ በእኔም መንገድ የተሰቃዩት፣ የተጋደሉትም፣ የተገደሉትም፣ ከእነሱ ኃጢአቶቻቸውን በእርግጥ አብሳለሁ፤ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውንም ገነቶች በእርግጥ አስገባቸዋለሁ።» (ይህ) ከአላህ ዘንድ የሆነ ምንዳ ነው። አላህም፣ እሱ ዘንድ መልካም ምንዳ አለ። (196) የእነዚያ የካዱት ሰዎች፣ በሀገር ውስጥ መዘዋወር አይሽወዳችሁ። (197) (ይህች) ጥቂት መጠቃቀሚያ ናት፤ ከዚያም መኖሪያቸው ገሀነም ናት፤ ምን ትክፋ ምንጣፍ! (198) ግን እነዚያ ጌታቸውን የፈሩ፣ ለእነሱ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች አሏቸው፤ በውስጧ ዘውታሪዎች ሲሆኑ ፤ (ይህም) ከአላህ ዘንድ የሆነ መስተንግዶ ነው። አላህ ዘንድም ያለው ነገር ለደጋጎቹ በላጭ ነው። (199) ከመጽሐፉም ባለቤቶች ወደ እናንተ በተወረደውና ወደ እነሱም በተወረደው (ቁርኣን) የሚያምኑ፣ ለአላህ ተዋራጆች ሆነው፣ በአላህ አንቀጾች ጥቂትን ዋጋ የማይለውጡ ሰዎች በእርግጥ አሉ። እነዚያ ለእነሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው። አላህ ምርመራው ፈጣን ነው። (200) እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ታገሱ፣ ታገሉ፣ ተከላከሉ፣ አላህንም ፍሩ፣ ትድኑ ዘንድ። (ሱረቱ አል-ኢምራን 3፡190-200) በሌላ ዘገባ፣ ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) ከእንቅልፋቸው በመነሳት ወደ ሰማይ በመመልከት የሱረቱ ሀል ኢምራንን የመጨረሻ ሩኩእ የመጀመሪያ አምስት አንቀጾችን ይቀሩ ነበር። [2]
Reference: [፩] ቡኻሪ፡ ፱፱፪ [፪] ሷሒሕ። ናሳኢ፡ ፩፮፳፮