Loading...
Language: Amharic
የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፣ "አንድ ባሪያ ኃጢአትን ከሰራ፣ ከዚያም በትክክል ዉዱ ካደረገ፣ ከዚያም ቆሞ ሁለት ረከአ ከሰገደ እና አላህን ምህረት ከጠየቀ፣ አላህ በእርግጥ ይምረዋል።" ከዚያም ይህንን አንቀጽ ቀሩ -
وَالَّذِينَ إِذَا فَعَلُوا فَاحِشَةً أَوْ ظَلَمُوا أَنفُسَهُمْ ذَكَرُوا اللَّهَ فَاسْتَغْفَرُوا لِذُنُوبِهِمْ وَمَن يَغْفِرُ الذُّنُوبَ إِلَّا اللَّهُ وَلَمْ يُصِرُّوا عَلَىٰ مَا فَعَلُوا وَهُمْ يَعْلَمُونَ ﴿١٣٥﴾ أُولَٰئِكَ جَزَاؤُهُم مَّغْفِرَةٌ مِّن رَّبِّهِمْ وَجَنَّاتٌ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا ۚ وَنِعْمَ أَجْرُ الْعَامِلِينَ ﴿١٣٦﴾
ወለዚነ ኢዛ ፈዐሉ ፋሂሸተን አው ዘለሙ አንፉሰሁም ዘከሩላሀ ፈስተግፈሩ ሊዙኑቢሂም ወመን የክፊሩዝ ዙኑበ ኢለላሁ ወለም ዩሲሩ ዐላ ማ ፈዐሉ ወሁም የዕለሙን። ኡላኢከ ጀዛኡሁም መግፊረቱም ሚር ረቢሂም ወጀናቱን ተጅሪ ሚን ተህቲሀል አንሀሩ ኻሊዲነ ፊሀ፤ ወኒዕመ አጅሩል ዐሚሊን።
(135) እነዚያም፣ መጥፎ ሥራን በሠሩ ወይም ነፍሶቻቸውን በበደሉ ጊዜ፣ አላህን የሚያስታውሱና ለኃጢአቶቻቸው ምህረትን የሚለምኑ፣ ኃጢአቶችንም ከአላህ ሌላ የሚምር ማን አለ? በሚሉት፣ በሠሩትም (ኃጢአት) ላይ እነሱ የሚያውቁ ሲሆኑ የማይዘወትሩ ናቸው። (136) እነዚህ ምንዳቸው ከጌታቸው የሆነ ምህረትና ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች ናቸው፤ በውስጧ ዘውታሪዎች ሲሆኑ፤ የሠሪዎችም ምንዳ ምን ያምር! (ሱረቱ አል ኢምራን 3፡135-136)
Reference: ሰሂህ (አልባኒ)። አቡ ዳውድ፡ ፲፭፻፳፩