Loading...
Language: Amharic
ረሱሉላህ (ሶ.ዐ.ወ) ተሽከርካሪ ላይ ሲሳፈሩ ቢስሚላህ ይሉ ነበር፣ ከተቀመጡ በኋላ የተቀረውን ይሉ ነበር፡
اَلْحَمْدُ لِلَّهِ، سُبْحَانَ الَّذِي سَخَّرَ لَنَا هَذَا وَمَا كُنَّا لَهُ مُقْرِنِيْنَ وَإِنَّا إِلَى رَبِّنَا لَمُنْقَلِبُوْنَ، اَلْحَمْدُ لِلَّهِ، اَلْحَمْدُ لِلَّهِ، اَلْحَمْدُ لِلَّهِ، اللَّهُ أَكْبَرُ، اللَّهُ أَكْبَرُ، اَللّهُ أَكْبَرُ، (لَا إِلٰهَ إِلَّا أَنْتَ) سُبْحَانَكَ، إِنِّي ظَلَمْتُ نَفْسِيْ فَاغْفِرْ لِي فَإِنَّهُ لَا يَغْفِرُ الذُّنُوْبَ إِلاَّ أَنْتَ
አልሀምዱ ሊላህ። ሱብሃነል-ለዚ ሰኸረ ለና ሀዛ ወ ማ ኩና ለሁ ሙቅሪኒን። ወ ኢና ኢላ ረቢና ለሙንቀሊቡን። አልሀምዱ ሊላህ፣ አልሀምዱ ሊላህ፣ አልሀምዱ ሊላህ፣ አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር፣ (ላ ኢላሀ ኢላ አንተ) ሱብሃነከ ኢኒ ዘለምቱ ነፍሲ ፈግፊር ሊ፣ ፈኢነሁ ላ የግፊሩዝ-ዙኑበ ኢላ አንተ
ምስጋና ለአላህ ይሁን። ይህን ላገራለልን ጌታ ጥራት ይገባው። እኛ ለእርሱ የምንችለው አልነበርንም። እኛም ወደ ጌታችን በእርግጥ ተመላሾች ነን። ምስጋና ለአላህ ይሁን፣ ምስጋና ለአላህ ይሁን፣ ምስጋና ለአላህ ይሁን። አላህ ከሁሉ በላይ ታላቅ ነው፣ አላህ ከሁሉ በላይ ታላቅ ነው፣ አላህ ከሁሉ በላይ ታላቅ ነው። ጥራት ይገባህ። አላህ ሆይ! እኔ ነፍሴን በደልኩ። ስለዚህ ማረኝ፣ ከአንተ በስተቀር ኃጢአትን የሚምር የለምና።
Reference: ሰሂህ (አልባኒ)። ቲርሚዚ፡ ፴፬፻፵፮