Loading...
Language: Amharic
أَسْتَوْدِعُ اللَّهَ دِيْنَكَ وَأَمَانَتَكَ وَخَوَاتِيْمَ عَمَلِكَ
አስተውዲኡላሃ ዲነከ፣ ወ አማነተከ፣ ወ ኸዋቲመ አመሊከ
ሃይማኖትህን፣ አደራህን እና የመጨረሻ ስራህን ለአላህ አደራ እሰጣለሁ (በአላህ ጥበቃ ስር እተዋለሁ)። አብዱላህ ኢብን ዑመር (ረ.ዐ) እንዲህ አሉ፡ የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) የስንብት ቃል ሲሰጡ፣ የሰውን እጅ ይዘው ሙሳፋሃ (ጨብጠው) ከላይ የተጠቀሰውን ዱዓ ይሉ ነበር። በሌላ ዘገባ፣ አብዱላህ ኢብን የዚድ ኸትሚ (ረ.ዐ)፣ የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) በእነዚህ ቃላት የስንብት ቃል ይሰጡ ነበር ብለዋል። ነገር ግን በዚህ ሁኔታ፣ ከነጠላ (ከ) ይልቅ የበዛ ቁጥር (ኩም) ተጠቅመዋል፡ “አስተውዲኡላሃ ዲነኩም ወ አማነተኩም ወ ኸዋቲመ አማሊኩም” ሃይማኖታችሁን፣ አደራችሁን እና የመጨረሻ ስራችሁን ለአላህ አደራ እሰጣለሁ።
Reference: ሰሂህ (አልባኒ)። ቲርሚዚ፡ ፴፬፻፵፫