Loading...
Language: Amharic
የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) በጉዞ ላይ በነበሩ ጊዜ ይህንን ዱዓ ይቀሩ ነበር፡
اَللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ فِي سَفَرِيْ هَذَا مِنَ الْبِرِّ وَالتَّقْوَى وَمِنَ الْعَمَلِ مَا تَرْضَى، اَللَّهُمَّ هَوِّنْ عَلَيْنَا الْمَسِيرَ وَاطْوِ عَنَّا بُعْدَ الْأَرْضِ اَللَّهُمَّ أَنْتَ الصَّاحِبُ فِي السَّفَرِ وَالْخَلِيفَةُ فِي الْأَهْلِ اَللَّهُمَّ اصْحَبْنَا فِي سَفَرِنَا وَاخْلُفْنَا فِي أَهْلِنَا
አላሁመ ኢኒ አስአሉከ ፊ ሰፈሪ ሀዛ ሚነል-ቢሪ ወት-ተቅዋ፣ ወ ሚነል-አመሊ ማ ተርዳ። አላሁመ ሀዊን አለይነል-መሲራ፣ ወጥዊ አና ቡእደል-አርድ። አላሁመ አንተስ-ሳሂቡ ፊስ ሰፈሪ ወል-ኸሊፈቱ ፊል-አህሊ። አላሁመ አስሀብና ፊ ሰፈሪና ወክሉፍና ፊ አህሊና
አላህ ሆይ፣ በዚህ ጉዟችን መልካምነትን እና አላህን መፍራትን፣ እንዲሁም የምትወደውን ስራ እንጠይቅሃለን። አላህ ሆይ፣ ጉዞውን በእኛ ላይ አግራራልን፣ የምድሩንም ርቀት አሳጥርልን። አላህ ሆይ፣ በጉዞ ላይ ጓደኛ በቤተሰብም ተተኪ ጠባቂ አንተ ነህ። አላህ ሆይ፣ በጉዟችን አብረኸን ሁን፣ ቤተሰቦቻችንንም ጠብቅ።
Reference: ሰሂህ (አልባኒ)። ቲርሚዚ፡ ፴፬፻፵፯