Loading...
Language: Amharic
ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) ጨምረው እንዲህ አሉ፡- ይህን የሚል ሰው፡-
أَسْتَغْفِرُ اللَّهَ الْعَظِيمَ الَّذِيْ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ وَأَتُوبُ إِلَيْهِ
አስተግፊሩላሀል አዚመል-ለዚ ላ ኢላሀ ኢላ ሁወል ሀዩል ቀዩሙ ወ አቱቡ ኢለይሂ
ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የሌለውን፣ ህያውና ራሱን ቻይ የሆነውን ታላቁን አላህ ምህረት እጠይቃለሁ፣ ወደ እርሱም እመለሳለሁ። ከግንባር ጦርነት በሸሸ ጊዜም እንኳን ቢሆን አላህ ይምረዋል።" [1] እሳቸው (ሶ.ዐ.ወ) አየህ አሉ፡- "ጌታ ወደ ባሪያው በጣም የሚቀርበው በሌሊቱ አጋማሽ ላይ ነው፣ ስለዚህ በዚያ ጊዜ አላህን ከሚያስታውሱት መሆን ከቻልክ፣ ሁን።" [2] እሳቸው (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህም አሉ፡- "አንድ ባሪያ ወደ ጌታው በጣም የሚቀርበው በሱጁድ ላይ እያለ ነው፣ ስለዚህ በዚያ ውስጥ ዱዓን አብዙ።" [3] እሳቸው (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህም አሉ፡- "በእርግጥ ልቤ ይሸፈናል፣ እና በእርግጥ እኔ የአላህን ምህረት በቀን መቶ ጊዜ እጠይቃለሁ።" [4]
Reference: [፩] ሰሂህ (አልባኒ)። አቡ ዳውድ፡ ፲፭፻፲፯ [፪] ሰሂህ (አልባኒ)። ቲርሚዚ፡ ፴፭፻፸፱ [፫] ሙስሊም፡ ፬፻፹፪ [፬] ሙስሊም፡ ፳፯፻፪