Loading...
Language: Amharic
رَبَّنَا تَقَبَّلْ مِنَّا ۖ إِنَّكَ أَنتَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ ﴿١٢٧﴾ رَبَّنَا وَاجْعَلْنَا مُسْلِمَيْنِ لَكَ وَمِن ذُرِّيَّتِنَا أُمَّةً مُّسْلِمَةً لَّكَ وَأَرِنَا مَنَاسِكَنَا وَتُبْ عَلَيْنَا ۖ إِنَّكَ أَنتَ التَّوَّابُ الرَّحِيمُ ﴿١٢٨﴾
ረበና ተቀበል ሚንና ኢንነከ አንተስ ሰሚዑል ዐሊም። ረበና ወጅዐልና ሙስሊመይኒ ለከ ወሚን ዙርሪያቲና ኡመተን ሙስሊመተል ለከ ወአሪና መናሲከና ወቱብ ዐለይና ኢንነከ አንተት ተዋቡር ረሂም።
(127) ጌታችን ሆይ! ከእኛ ተቀበል። አንተ ሰሚው አዋቂው ነህና። (128) ጌታችን ሆይ! ለአንተ ታዛዦችም አድርገን። ከዘሮቻችንም ለአንተ ታዛዥ ህዝቦችን (አድርግ)። የሐጅ ስነስርዓቶቻችንንም አሳየን። በላያችንም ተመለስልን። አንተ ጸጸትን ተቀባዩ አዛኙ ነህና።
Reference: ሱራ አል-በቀራህ ፪:፻፳፯-፻፳፰