Loading...
Language: Amharic
رَبَّنَا وَسِعْتَ كُلَّ شَيْءٍ رَّحْمَةً وَعِلْمًا فَاغْفِرْ لِلَّذِينَ تَابُوا وَاتَّبَعُوا سَبِيلَكَ وَقِهِمْ عَذَابَ الْجَحِيمِ ﴿٧﴾ رَبَّنَا وَأَدْخِلْهُمْ جَنَّاتِ عَدْنٍ الَّتِي وَعَدتَّهُمْ وَمَن صَلَحَ مِنْ آبَائِهِمْ وَأَزْوَاجِهِمْ وَذُرِّيَّاتِهِمْ ۚ إِنَّكَ أَنتَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ ﴿٨﴾ وَقِهِمُ السَّيِّئَاتِ ۚ وَمَن تَقِ السَّيِّئَاتِ يَوْمَئِذٍ فَقَدْ رَحِمْتَهُ ۚ وَذَٰلِكَ هُوَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ ﴿٩﴾
ረበና ወሲዕተ ኩለ ሸይኢር ራህመተን ወዒልመን ፈግፊር ሊለዚነ ታቡ ወተበዑ ሰቢለከ ወቂሂም ዐዛበል ጀሂም። ረበና ወአድኺልሁም ጀናቲ ዐድኒኒለቲ ወዐድተሁም ወመን ሷለሀ ሚን አባኢሂም ወአዝዋጂሂም ወዙርሪያቲሂም፤ ኢንነከ አንተል ዐዚዙል ሀኪም። ወቂሂሙስ ሰይይአት፤ ወመን ተቂስ ሰይይአቲ የውመኢዚን ፈቀድ ረሂምተህ፤ ወዛሊከ ሁወል ፈውዙል ዐዚም።
ጌታችን ሆይ! ነገሩን ሁሉ በእዝነትና በእውቀት አዳርሰሃል። ለነዚያ ለተጸጸቱት መንገዳህንም ለተከተሉት ማርላቸው። የገሃነምንም ቅጣት ጠብቃቸው። (7) ጌታችን ሆይ! በገነት አድንም አግባቸው። ያቺን የቀጠርካቸውን፤ ከአባቶቻቸውም፣ ከሚስቶቻቸውም፣ ከዘሮቻቸውም የመልካም የሰሩትን (አግባቸው)። አንተ አሸናፊው ጥበበኛው አንተ ብቻ ነህና። (8) መጥፎ ስራዎችንም ጠብቃቸው። በዚያ ቀንም መጥፎ ስራዎችን (ቅጣታቸውን) የጠበቀው ሰው፣ በርግጥ አዘንክለት። ይህም እርሱ ታላቅ እድል ነው። (9)
Reference: ሱራ ጋፊር ፵:፯-፱