Loading...
Language: Amharic
ኢብን አባስ (ረ.ዐ) እንዲህ አሉ፡ የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) በአደጋ ወይም በችግር ጊዜ እነዚህን ቃላት ይሉ ነበር፡
لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ، الْعَظِيْمُ الْحَلِيْمُ لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ، رَبُّ الْعَرْشِ الْعَظِيْمِ لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ، رَبُّ السَّمَاوَاتِ، وَرَبُّ الْأَرْضِ، وَرَبُّ الْعَرْشِ الْكَرِيمِ
ላ ኢላሀ ኢለላሁል-አዚሙል-ሀሊም፣ ላ ኢላሀ ኢለላሁ ረቡል-አርሺል-አዚም፣ ላ ኢላሀ ኢለላሁ ረቡስ-ሰማዋቲ ወ ረቡል-አርዲ ወ ረቡል-አርሺል-ከሪም
ከታላቁ እና ታጋሹ አላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም። ከታላቁ ዙፋን ጌታ አላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም። ከሰማያት ጌታ፣ ከምድር ጌታ እና ከክቡር ዙፋን ጌታ አላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም።
Reference: ቡኻሪ ፯፬፫፩