Loading...
Language: Amharic
ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) በአደጋ ጊዜ፣ እንዲህ ይሉ ነበር -
لَا إِلَهَ إِلاَّ أَنْتَ سُبْحَانَكَ إِنِّى كُنْتُ مِنَ الظَّالِمِيْنَ
ላ ኢላሀ ኢላ አንተ ሱብሀነከ ኢኒ ኩንቱ ሚነዝ ዛሊሚን
ከአንተ በስተቀር ሊመለክ የሚገባው (አምላክ) የለም፣ ጥራት ይገባህ። እኔ በእርግጥ ከበደለኞች ነበርኩ። ኢብራሂም ቢን ሙሐመድ ቢን ሰእድ ከአባታቸው፣ ከሰእድ እንደዘገቡት የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡- “ዙን-ኑን (ነቢዩ ዩኑስ) በዓሣ ነባሪ ሆድ ውስጥ ሳሉ ያደረጉት ጸሎት፡ ‘ከአንተ በስተቀር የሚመለክ የለም፣ ጥራት ይገባህ፣ እኔ በእርግጥ ከበደለኞች ነበርኩ። (ላ ኢላሀ ኢላ አንተ ስብሀነከ ኢኒ ኩንቱ ሚነዝ-ዛሊሚን)’ በእርግጥ፣ አንድ ሙስሊም ሰው ለማንኛውም ነገር በዚህ አይለምንም፣ መቼም ቢሆን፣ አላህ ለእርሱ የሚመልስለት ቢሆን እንጂ።” ጃሚእ አት-ቲርሚዚ 3505 [ሶሂህ (አልባኒ)። ቲርሚዚ፡ 3505]
Reference: ሷሒሕ። ቲርሚዚ፡ ፫፭፰፭