Loading...
Language: Amharic
ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ሌሊት ከእንቅልፉ የነቃ እና እነዚህን ቃላት የተናገረ ሰው -
لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ وَحْدَهُ لَا شَرِيكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَىْءٍ قَدِيرٌ اَلْحَمْدُ لِلَّهِ وَسُبْحَانَ اللَّهِ وَلَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ وَاللَّهُ أَكْبَرُ وَلَا حَوْلَ وَلَا قُوَّةَ إِلَّا بِاللَّهِ
ላ ኢላሀ ኢለላሁ ወህደሁ ላ ሸሪከ ለሁ፣ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሀምድ፣ ወ ሁወ አላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር። አልሀምዱሊላሂ፣ ወ ሱብሀነላሂ፣ ወ ላ ኢላሀ ኢለላሁ፣ ወላሁ አክበር፣ ወ ላ ሀውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ
ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ እርሱ ብቻውን ነው፤ ተጋሪ የለውም። ንግስና የርሱ ነው፤ ምስጋናም የርሱ ነው። እርሱ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው። ምስጋና ለአላህ ይሁን። አላህ ጥራት ይገባው። ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም። አላህ ታላቅ ነው። ከአላህ በስተቀር ምንም ኃይልም ሆነ ጉልበት የለም። ከዚያም፡- «አላህ ሆይ! ማረኝ» ካለ፣ ወይም (አላህን) ከለመነ፣ ምላሽ ይሰጠዋል። ዉዱእ አድርጎ (ከሰገደም)፣ ሶላቱ ተቀባይነት ያገኛል።
Reference: ቡኻሪ፡ ፲፩፻፶፬