Loading...
Language: Amharic
በአቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንደተረከው፣ የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- "በእርግጥ አላህ ማስነጠስን ይወዳል፣ ማዛጋትን ይጠላል። ስለዚህ ከእናንተ አንዱ ካስነጠሰ እና 'አል-ሃምዱሊላህ (ምስጋና ለአላህ ይሁን)' ካለ፣ ለሰማው ሁሉ፡ 'የርሀሙከላህ (አላህ ይዘንልህ)' ማለቱ ግዴታ ነው። ስለ ማዛጋት ግን፣ ከእናንተ አንዱ ሲያዛጋ በተቻለው መጠን ይቆጠብ እና፡ "ሀ ሀ' አይበል፤ ያ ሰይጣን በእርሱ ስለሚስቅበት ነው።"
Reference: ቡኻሪ፡ ፴፪፻፹፱