Loading...
Language: Amharic
ማንኛውም የአላህ ባሪያ ከባድ ችግር ሲደርስበት (እንዲህ ብሎ) ከጸለየ -
إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّا إِلَيْهِ رَاجِعُوْنَ، اَللَّهُمَّ أْجُرْنِيْ فِي مُصِيْبَتِيْ وَأَخْلِفْ لِي خَيْرًا مِّنْهَا
ኢና ሊላሂ ወ ኢና ኢለይሂ ራጂዑን፣ አላሁመ-እጁርኒ ፊ ሙሲበቲ ወ አኽሊፍ ሊ ኸይረን ሚንሀ
እኛ የአላህ ነን፤ ወደርሱም ተመላሾች ነን። አላህ ሆይ፣ በችግሬ ውስጥ ምንዳን ስጠኝ፤ ከእርሷም የተሻለን ለእኔ ተካልኝ። ኡሙ ሰለማ (ረ.ዐ) እንደተረኩት የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ማንኛውም ሙስሊም ከባድ ችግር ሲደርስበት አላህ ያዘዘውን (ዱዓው ከላይ ተጠቅሷል) ካለ፣ አላህ ከዚያ (ከጠፋበት ነገር) የተሻለን በምትኩ ይሰጠዋል።
Reference: ሙስሊም፡ ፱፻፲፰