Loading...
Language: Amharic
ኡሙ ሰለማ (ረ.ዐ) እንደዘገቡት፡- የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) ወደ አቡ ሰለማ (በሞቱ ጊዜ) መጡ። አይኖቹ ፈጠው ክፍት ነበሩ። እሳቸውም ጨፈኗቸው፤ ከዚያም እንዲህ አሉ፡- «ነፍስ በተወሰደች ጊዜ፣ እይታ ይከተላታል።» ከቤተሰቦቹ መካከል የተወሰኑት አለቀሱ እና ዋይ አሉ (ጮኹ)። ስለዚህ እንዲህ አሉ፡- «ለራሳችሁ ከመልካም ነገር በስተቀር አትለምኑ (አትጸልዩ)፤ መላእክት ለምትሉት ነገር “አሜን” ይላሉና።»
Reference: ሙስሊም፡ ፱፻፳