Loading...
Language: Amharic
ከአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) ጋር በመስገድ ላይ እያሉ፣ ከሰዎች መካከል አንዱ እንዲህ አለ -
اَللَّهُ أَكْبَرُ كَبِيْرًا وَالْحَمْدُ لِلَّهِ كَثِيْرًا وَسُبْحَانَ اللَّهِ بُكْرَةً وَأَصِيْلًا
አላሁ አክበር ከቢረን፣ ወልሀምዱ ሊላሂ ከሲረን፣ ወ ሱብሀነላሂ ቡክረተን ወ አሲላ
አላህ እጅግ ታላቅ ነው፤ ምስጋናም ብዙ ለአላህ ነው። በጠዋትና በማታ አላህ ጥራት ይገባው። የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡- «እንደዚህ እና እንደዚህ ያለ ቃል የተናገረው ማነው?» ከሰዎች መካከል አንዱ ሰው (እነዚህን ቃላት የቀራው)፡- «እኔ ነኝ፣ የአላህ መልእክተኛ ሆይ» አለ። እሳቸውም (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡- «አባባሉ አስደነቀኝ፤ የሰማይ በሮች ለእርሱ ተከፍተውለታልና።» ኢብን ዑመር (ረ.ዐ) እንዲህ አሉ፡- «የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) ይህንን ሲሉ ከሰማሁ በኋላ (እነዚህን ቃላት) አልተውኳቸውም።»
Reference: ሙስሊም፡ ፮፻፩