Loading...
Language: Amharic
አነስ (ረ.ዐ) እንደዘገቡት፡- አንድ ሰው እያለከለከ መጣ እና ወደ ሰጋጆች ሰልፍ ገባ፤ እንዲህም አለ፡-
اَلْحَمْدُ لِلَّهِ حَمْدًا كَثِيْرًا طَيِّبًا مُبَارَكًا فِيهِ
አልሀምዱሊላሂ ሀምደን ከሲረን ጠይበን ሙባረከን ፊህ
ምስጋና ለአላህ ይሁን፤ ብዙ፣ መልካም እና የተባረከ ምስጋና። የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) ሶላቱን በጨረሱ ጊዜ እንዲህ አሉ፡- «ከእናንተ መካከል እነዚህን ቃላት የተናገረው ማነው?» ሰዎቹ ዝም አሉ። እሳቸውም (ነቢዩ ሶ.ዐ.ወ) እንደገና፡- «ከእናንተ መካከል እነዚህን ቃላት የተናገረው ማነው? ምንም መጥፎ ነገር አልተናገረም» አሉ። ከዚያም አንድ ሰው፡- «እኔ መጣሁኝ እና ለመተንፈስ ተቸግሬ ነበር፣ ስለዚህ ተናገርኳቸው» አለ። እሳቸውም መለሱ፡- «አስራ ሁለት መላእክት (ወደ አላህ) ማን እንደሚወስዳቸው እርስ በርስ ሲፋጠጡ አየሁ።»
Reference: ሙስሊም፡ ፬፻