Loading...
Language: Amharic
ረሱሉላህ (ሶ.ዐ.ወ) በሚሳፈሩበት ጊዜ ቢስሚላህ ይሉ ነበር፣ ከተቀመጡ በኋላ የቀረውን ዱዓ ይሉ ነበር፡
اَلْحَمْدُ لِلَّهِ، سُبْحَانَ الَّذِي سَخَّرَ لَنَا هَذَا وَمَا كُنَّا لَهُ مُقْرِنِينَ وَإِنَّا إِلَى رَبِّنَا لَمُنْقَلِبُونَ، اَلْحَمْدُ لِلَّهِ، اَلْحَمْدُ لِلَّهِ، اَلْحَمْدُ لِلَّهِ، اَللَّهُ أَكْبَرُ، اَللَّهُ أَكْبَرُ، اَللَّهُ أَكْبَرُ، (لَا إِلَهَ إِلَّا أَنْتَ) سُبْحَانَكَ، إِنِّي ظَلَمْتُ نَفْسِيْ فَاغْفِرْ لِي فَإِنَّهُ لَا يَغْفِرُ الذُّنُوْبَ إِلَّا أَنْتَ
አልሀምዱ ሊላህ። ሱብሃነለዚ ሰኸረ ለና ሀዛ ወ ማ ኩና ለሁ ሙቅሪኒን። ወ ኢና ኢላ ረቢና ለሙንቀሊቡን። አልሀምዱ ሊላህ፣ አልሀምዱ ሊላህ፣ አልሀምዱ ሊላህ፣ አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር፣ (ላ ኢላሀ ኢላ አንተ) ሱብሃነከ ኢኒ ዘለምቱ ነፍሲ ፈግፊርሊ፣ ፈኢነሁ ላ የግፊሩዝ-ዙኑበ ኢላ አንተ
ምስጋና ለአላህ ይሁን። ይህንን ለእኛ የገራን ጌታ ጥራት ይገባው፤ እኛ ለእርሱ (ለመገዛት) ችሎታ አልነበረንም። እኛም ወደ ጌታችን ተመላሾች ነን። ምስጋና ለአላህ ይሁን (3 ጊዜ)፣ አላህ ታላቅ ነው (3 ጊዜ)፣ ጥራት ይገባህ። አላህ ሆይ፣ እኔ ነፍሴን በደልኩ። ማረኝ፣ ምክንያቱም ከአንተ ሌላ ኃጢአትን የሚምር የለምና።
Reference: ሷሒሕ። ቲርሚዚ፡ ፫፬፵፮