Loading...
Language: Amharic
አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንደዘገቡት፡- የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- «የቁርአን እናት (ኡሙል ቁርአን - ፋቲሃ) ያልተቀራበትን ሶላት የሰገደ ሰው፣ ሶላቱ ጎደሎ ናት [ይህንን ሶስት ጊዜ አሉ] እና ሙሉ አይደለችም።» ለአቡ ሁረይራ (ረ.ዐ)፡- «አንዳንድ ጊዜ ከኢማሙ ኋላ እንሆናለን?» ተባሉ። እሳቸውም እንዲህ አሉ፡- «ለራሳችሁ (በውስጣችሁ) ቅሯት፤ ምክንያቱም የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ ሲሉ ሰምቻለሁና፡- “ሶላትን በኔና በባሪያዬ መካከል ለሁለት ከፍያለሁ፤ ለባሪያዬም የጠየቀው አለ።” ባሪያው፡- “አልሀምዱሊላሂ ረቢል አለሚን (ምስጋና ለአላህ ይሁን፣ የዓለማት ጌታ)” ሲል፣ ልዑሉ አላህ፡- “ባሪያዬ አመሰገነኝ” ይላል። (ባሪያው)፡- “አር-ራህመር ራሂም (እጅግ በጣም ሩኅሩህ፣ በጣም አዛኝ)” ሲል፣ ልዑሉ አላህ፡- “ባሪያዬ አወደሰኝ” ይላል። (ባሪያው)፡- “ማሊኪ ያውሚዲን (የፍርድ ቀን ባለቤት)” ሲል፣ እርሱ (አላህ)፡- “ባሪያዬ አከበረኝ” ይላል። እና አንዳንዴም፡- “ባሪያዬ (ጉዳዩን) ለእኔ ሰጠ” ይላል። (ሰጋጁ)፡- “ኢያከ ናዕቡዱ ወ ኢያከ ነስታዒን (አንተን ብቻ እንገዛለን፣ አንተንም ብቻ እርዳታ እንጠይቃለን)” ሲል፣ እርሱ (አላህ)፡- “ይህ በኔና በባሪያዬ መካከል ነው፤ ለባሪያዬም የጠየቀው አለው” ይላል። ከዚያም (ሰጋጁ)፡- “ኢህዲነስ ሲራጠል ሙስተቂም፣ ሲራጠለዚነ አንአምተ አለይሂም፣ ገይሪል መግዱቢ አለይሂም ወለድ-ዷሊን (ወደ ቀጥተኛው መንገድ ምራን፣ የነዚያን በነርሱ ላይ ጸጋህን የለገስክላቸውን ሰዎች መንገድ፣ (በነርሱ ላይ) የተቆጣህባቸውን እና የጠመሙትን መንገድ ያልሆነውን)” ሲል፣ እርሱ (አላህ)፡- “ይህ ለባሪያዬ ነው፣ ለባሪያዬም የጠየቀው አለው” ይላል።»
Reference: ሙስሊም፡ ፫፻፺፭