Loading...
Language: Amharic
አነስ ኢብኑ ማሊክ እንደተረኩት፡ እንዲህ አሉ፡ "ከአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) ጋር ነበርን፣ በአንድ ወቅት ዝናብ በላያችን ላይ መዝነብ ጀመረ። ከዚያም የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) የተወሰነ የልብሳቸውን ክፍል አነሱ የዝናቡ ውሃ በላያቸው ላይ እንዲወድቅ። እኛም እንዲህ ብለን ጠየቅን፣ “የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ለምን እንዲህ አደረጉ?” እርሳቸውም፣ "አሁን ከታላቁ ጌታው የመጣ ነውና!" አሉን።"
Reference: ሙስሊም፡ ፰፻፺፰