Loading...
Language: Amharic
አንድ ቀን ከነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) በኋላ እየሰገድን ነበር። ከሩኩዕ ሲነሱ፡- «ሰሚአላሁ ሊመን ሀሚደህ» አሉ። ከኋላቸው ያለ አንድ ሰው እንዲህ አለ -
رَبَّنَا وَلَكَ الْحَمْدُ، حَمْدًا كَثِيْرًا طَيِّبًا مُبَارَكًا فِيهِ
ረበና ወ ለከል-ሀምድ፣ ሀምደን ከሲረን ጠይበን ሙባረከን ፊህ
ጌታችን ሆይ፣ ምስጋና ለአንተ ይሁን፤ ብዙ፣ መልካም እና የተባረከ ምስጋና። ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) ሶላቱን ሲጨርሱ፡- «እነዚህን ቃላት የተናገረው ማነው?» ብለው ጠየቁ። ሰውየውም፡- «እኔ» አለ። ነቢዩም (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡- «ከሠላሳ በላይ መላእክት (ይህንን አባባል) ማን ቀድሞ እንደሚጽፈው ሲሽቀዳደሙ አየሁ።»
Reference: ቡኻሪ፡ ፯፻፺፱