Loading...
Language: Amharic
ሱራ ኢኽላስ
بِسْمِ اللَّـهِ الرَّحْمَـٰنِ الرَّحِيمِ قُلْ هُوَ اللَّـهُ أَحَدٌ ﴿١﴾ اللَّـهُ الصَّمَدُ ﴿٢﴾ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ ﴿٣﴾ وَلَمْ يَكُن لَّهُ كُفُوًا أَحَدٌ ﴿
ቢስሚላሂር-ራህማኒር-ረሂም። (1) ቁል ሁወላሁ አሀድ። (2) አላሁስ-ሰመድ። (3) ለም የሊድ ወ ለም ዩለድ። (4) ወ ለም የኩን ለሁ ኩፉወን አሀድ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፣ በጣም አዛኝ በሆነው። (1) በል፤ እርሱ አላህ አንድ ነው። (2) አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው። (3) አልወለደም፣ አልተወለደምም። (4) ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም። (ሱራ ኢኽላስ 1-4) ሱራ አል-ፈለቅ ቢስሚላሂር-ራህማኒር-ረሂም። (1) ቁል አኡዙ ቢረቢል-ፈለቅ። (2) ሚን ሸሪ ማ ኸለቅ። (3) ወ ሚን ሸሪ ጋሲቂን ኢዛ ወቀብ። (4) ወ ሚን ሸሪን-ነፋሳቲ ፊል-ኡቀድ። (5) ወ ሚን ሸሪ ሀሲዲን ኢዛ ሀሰድ በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፣ በጣም አዛኝ በሆነው። (1) በል፤ በገለባው ጌታ እጠበቃለሁ። (2) ከፈጠረው ፍጡር ክፋት። (3) ከጨለማም ክፋት በገባ ጊዜ። (4) በቋጠሮዎችም ላይ ተፋዎች ከሆኑት (ጠንቋዮች) ክፋት። (5) ከምቀኛም ክፋት በምቀኝነት ጊዜ። (ሱራ አል-ፈለቅ 1-5) ሱራ አን-ናስ ቢስሚላሂር-ራህማኒር-ረሂም። (1) ቁል አኡዙ ቢረቢን-ናስ። (2) መሊኪን-ናስ። (3) ኢላሂን-ናስ። (4) ሚን ሸሪል-ወስዋሲል-ኸናስ። (5) አለዚ ዩወስዊሱ ፊ ሱዱሪን-ናስ። (6) ሚነል-ጂነቲ ወን-ናስ በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፣ በጣም አዛኝ በሆነው። (1) በል፤ በሰዎች ጌታ እጠበቃለሁ። (2) በሰዎች ንጉሥ። (3) በሰዎች አምላክ። (4) ከአስሾላኪው ጎትቋች (ሰይጣን) ክፋት። (5) ከዚያ በሰዎች ልቦች ውስጥ የሚጎተጉት ከሆነው። (6) ከጂኒዎችም ከሰዎችም (ከሆነው ጎትቋች፤ እጠበቃለሁ በል)። (ሱራ አል-ናስ 1-6)
Reference: ቡኻሪ፡ ፶፯፻፴፭