Loading...
Language: Amharic
አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንደዘገቡት፡- ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- «ኢማሙ ሲል እናንተም “አሜን” በሉ፤ ምክንያቱም የርሱ “አሜን” ማለት ከመላእክት ጋር የገጠመለት ሰው፣ ያለፈው ኃጢአቱ ሁሉ ይማርለታል።» [፩] በሌላ ዘገባ አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንደዘገቡት፡- የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- «ኢማሙ “ገይሪል መግዱቢ አለይሂም ወለድ-ዷሊን” (በነርሱ ላይ የተቆጣህባቸውን እና የጠመሙትን መንገድ አይደለም) በሚልበት ጊዜ “አሜን” በሉ፤ ምክንያቱም አባባሉ (አሜን ማለቱ) ከመላእክት ጋር የገጠመለት ሰው፣ ያለፈው ኃጢአቱ ሁሉ ይማርለታል።» [፪]
Reference: [፩] ቡኻሪ፡ ፯፻፹ [፪] ቡኻሪ፡ ፯፻፹፪