Loading...
Language: Amharic
بِسْمِ اللَّهِ أَرْقِيْكَ مِنْ كُلِّ شَيْءٍ يُؤْذِيْكَ، مِنْ شَرِّ كُلِّ نَفْسٍ أَوْ عَيْنٍ حَاسِدٍ، اَللَّهُ يَشْفِيكْ، بِسْمِ اللَّهِ أَرْقِيْكَ
ቢስሚላሂ አርቂክ፣ ሚን ኩሊ ሸይኢን ዩእዚክ፣ ሚን ሸሪ ኩሊ ነፍሲን አው አይኒን ሃሲዲን። አላሁ የሽፊክ፣ ቢስሚላሂ አርቂክ
በአላህ ስም ሩቅያህ አደርግልሃለሁ፣ ከሚጎዳህ ነገር ሁሉ፣ ከማንኛውም ነፍስ ወይም ምቀኛ ዓይን ክፋት፣ አላህ ይፈውስህ። በአላህ ስም ሩቅያህ አደርግልሃለሁ። አቡ ሰኢድ አል-ኹድሪ (ረ.ዐ) ጂብሪል (ዐ.ሰ) ወደ አላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) መጡ (ያኔ እሳቸው ትኩሳት ነበረባቸው፣ ታመው ነበር)። ጂብሪል (ዐ.ሰ)፡- ሙሐመድ ሆይ ታመሃልን? አላቸው። እሳቸውም፡- አዎ አሉ። ከዚያም ከላይ ያሉትን ቃላት ተናገረ።
Reference: ሙስሊም፡ ፳፩፻፹፮