Loading...
Language: Amharic
الم ﴿١﴾ ذَٰلِكَ الْكِتَابُ لَا رَيْبَ ۛ فِيهِ ۛ هُدًى لِّلْمُتَّقِينَ ﴿٢﴾ الَّذِينَ يُؤْمِنُونَ بِالْغَيْبِ وَيُقِيمُونَ الصَّلَاةَ وَمِمَّا رَزَقْنَاهُمْ يُنفِقُونَ ﴿٣﴾ وَالَّذِينَ يُؤْمِنُونَ بِمَا أُنزِلَ إِلَيْكَ وَمَا أُنزِلَ مِن قَبْلِكَ وَبِالْآخِرَةِ هُمْ يُوقِنُونَ ﴿٤﴾ أُولَـٰئِكَ عَلَىٰ هُدًى مِّن رَّبِّهِمْ ۖ وَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْمُفْلِحُونَ ﴿٥﴾
አሊፍ ላም ሚም። ዛሊከል ኪታቡ ላ ረይበ ፊህ፤ ሁደል ሊል ሙተቂን። አለዚነ ዩእሚኑነ ቢል ገይቢ ወዩቂሙነስ ሰላተ ወሚማ ረዘቅናሁም ዩንፊቁን። ወለዚነ ዩእሚኑነ ቢማ ኡንዚለ ኢለይከ ወማ ኡንዚለ ሚን ቀብሊከ ወቢል አኺረቲ ሁም ዩቂኑን። ኡላኢከ ዐላ ሁደም ሚር ረቢሂም ወኡላኢከ ሁሙል ሙፍሊሁን።
(1) አሊፍ፣ ላም፣ ሚም፣ (2) ይህ መጽሐፍ (ከአላህ መሆኑ) ጥርጥር የለበትም፤ ለፈራህያን (ለአላህ ተገዢዎች) መሪ ነው። (3) ለነዚያ በሩቁ ነገር የሚያምኑ፣ ሶለትንም ደንቡን ጠብቀው የሚሰግዱ፣ ከሰጠናቸውም ሲሳይ የሚለግሱ፤ (4) ለነዚያም ወደ አንተ በተወረደውና ከአንተ በፊትም በተወረደው የሚያምኑ፣ በመጨረሻይቱም (ዓለም) እነሱ የሚያረጋግጡ ለሆኑት (መሪ ነው)። (5) እነዚያ ከጌታቸው በሆነ መሪ ላይ ናቸው፤ እነዚያም እነሱ የፈለጉትን የሚያገኙ ናቸው። (ሱረቱ አል-በቀራ፡ 1-5)
Reference: ሱራ አል-በቀራህ ፪: ፩-፭