Loading...
Language: Amharic
لِّلَّـهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ ۗ وَإِن تُبْدُوا مَا فِي أَنفُسِكُمْ أَوْ تُخْفُوهُ يُحَاسِبْكُم بِهِ اللَّـهُ ۖ فَيَغْفِرُ لِمَن يَشَاءُ وَيُعَذِّبُ مَن يَشَاءُ ۗ وَاللَّـهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ ﴿٢٨٤﴾ آمَنَ الرَّسُولُ بِمَا أُنزِلَ إِلَيْهِ مِن رَّبِّهِ وَالْمُؤْمِنُونَ ۚ كُلٌّ آمَنَ بِاللَّـهِ وَمَلَائِكَتِهِ وَكُتُبِهِ وَرُسُلِهِ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِّن رُّسُلِهِ ۚ وَقَالُوا سَمِعْنَا وَأَطَعْنَا ۖ غُفْرَانَكَ رَبَّنَا وَإِلَيْكَ الْمَصِيرُ ﴿٢٨٥﴾ لَا يُكَلِّفُ اللَّـهُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَا ۚ لَهَا مَا كَسَبَتْ وَعَلَيْهَا مَا اكْتَسَبَتْ ۗ رَبَّنَا لَا تُؤَاخِذْنَا إِن نَّسِينَا أَوْ أَخْطَأْنَا ۚ رَبَّنَا وَلَا تَحْمِلْ عَلَيْنَا إِصْرًا كَمَا حَمَلْتَهُ عَلَى الَّذِينَ مِن قَبْلِنَا ۚ رَبَّنَا وَلَا تُحَمِّلْنَا مَا لَا طَاقَةَ لَنَا بِهِ ۖ وَاعْفُ عَنَّا وَاغْفِرْ لَنَا وَارْحَمْنَا ۚ أَنْتَ مَوْلَانَا فَانْصُرْنَا عَلَى الْقَوْمِ الْكَافِرِينَ ﴿٢٨٦﴾
ሊላሂ ማ ፊስ ሰማዋቲ ወማ ፊል አርድ፤ ወኢን ቱብዱ ማ ፊ አንፉሲኩም አው ቱኽፉሁ ዩሀሲብኩም ቢሂላህ፤ ፈየግፊሩ ሊመን የሻኡ ወዩዐዚቡ መን የሻእ፤ ወላሁ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር። አመነር ረሱሉ ቢማ ኡንዚለ ኢለይሂ ሚር ረቢሂ ወል ሙእሚኑን፤ ኩሉን አመነ ቢላሂ ወመላኢከቲሂ ወኩቱቢሂ ወሩሱሊሂ ላ ኑፈሪቁ በይነ አሀዲም ሚር ሩሱሊህ፤ ወቃሉ ሰሚዕና ወአጠዕና ጉፍራነከ ረበና ወኢለይከል መሲር። ላ ዩከሊፉላሁ ነፍሰን ኢላ ውስዐሀ፤ ለሀ ማ ከሰበት ወዐለይሀ መክተሰበት፤ ረበና ላ ቱአኺዝና ኢን ነሲና አው አኽጠእና፤ ረበና ወላ ተህሚል ዐለይና ኢስረን ከማ ሀመልተሁ ዐለለዚነ ሚን ቀብሊና፤ ረበና ወላ ቱሀሚልና ማ ላ ጣቀተ ለና ቢህ፤ ወዕፉ ዐንና ወግፊር ለና ወርሀምና፤ አንተ መውላና ፈንሱርካ ዐለል ቀውሚል ካፊሪን።
(284) በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው፤ በነፍሶቻችሁ ውስጥ ያለውን ነገር ብትገልጹ ወይም ብትደብቁት አላህ በሱ ይቆጣጠራችኋል፤ ለሚሻውም ሰው ይምራል፤ የሚሻውንም ይቀጣል፤ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው። (285) መልእክተኛው ከጌታው ወደርሱ በተወረደው አመነ፤ አማኞችም (እንደዚሁ)፤ ሁሉም በአላህ፣ በመላእክቱም፣ በመጻሕፍቱም፣ በመልእክተኞቹም «ከመልእክተኞቹ በአንድም መካከል አንለይም» (የሚሉ ሲሆኑ) አመኑ፤ «ሰማን ታዘዝንም፤ ጌታችን ሆይ! ምህረትህን (እንሻለን)፤ መመለሻም ወደ አንተ ነው» አሉ። (286) አላህ ነፍስን ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም፤ ለርሷ (ከመልካም ስራ) የሰራችው አለላት፤ በርሷም ላይ (ከክፉ) ያፈራችው አለባት፤ (በሉ)፡- «ጌታችን ሆይ! ብንረሳ ወይም ብንሳሳት አትይዘን (አትቅጣን)፤ ጌታችን ሆይ! ከባድ ሸክምንም ከኛ በፊት በነበሩት ላይ እንደጫንከው በኛ ላይ አትጫንብን፤ ጌታችን ሆይ! ለኛም በሱ አቅም የሌለንን ነገር አታሸክመን፤ ይቅር በለን፣ ማረን፣ እዘንልንም፣ አንተ ረዳታችን ነህ፤ በከሃዲዎች ህዝቦች ላይም እርዳን።» (ሱረቱ አል-በቀራ፡ 284-286)
Reference: ሱራ አል-በቀራህ ፪: ፪፻፹፬-፪፻፹፮