Loading...
Language: Amharic
إِنَّ رَبَّكُمُ اللَّـهُ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ ثُمَّ اسْتَوَىٰ عَلَى الْعَرْشِ يُغْشِي اللَّيْلَ النَّهَارَ يَطْلُبُهُ حَثِيثًا وَالشَّمْسَ وَالْقَمَرَ وَالنُّجُومَ مُسَخَّرَاتٍ بِأَمْرِهِ ۗ أَلَا لَهُ الْخَلْقُ وَالْأَمْرُ ۗ تَبَارَكَ اللَّـهُ رَبُّ الْعَالَمِينَ ﴿٥٤﴾ ادْعُوا رَبَّكُمْ تَضَرُّعًا وَخُفْيَةً ۚ إِنَّهُ لَا يُحِبُّ الْمُعْتَدِينَ ﴿٥٥﴾ وَلَا تُفْسِدُوا فِي الْأَرْضِ بَعْدَ إِصْلَاحِهَا وَادْعُوهُ خَوْفًا وَطَمَعًا ۚ إِنَّ رَحْمَتَ اللَّـهِ قَرِيبٌ مِّنَ الْمُحْسِنِينَ ﴿٥٦﴾
ኢንነ ረበኩሙላሁለዚ ኸለቀስ ሰማዋቲ ወል አርዳ ፊ ሲተቲ አያሚን ሱመስተዋ ዐለል ዐርሺ ዩግሺል ለይለን ነሀረ የጥሉቡሁ ሀሲሰን ወሸምሰ ወልቀመረ ወኑጁመ ሙሰኸራቲም ቢአምሪህ፤ አላ ለሁል ኸልቁ ወል አምር፤ ተባረከላሁ ረቡል ዐለሚን። ኡድዑ ረበኩም ተዶሩዐን ወኹፍየህ፤ ኢንነሁ ላ ዩሂቡል ሙዕተዲን። ወላ ቱፍሲዱ ፊል አርዲ ባዕደ ኢስላሂሀ ወድዑሁ ኸውፈን ወጠመዐ፤ ኢንነ ራህመተላሂ ቀሪቡም ሚነል ሙህሲኒን።
(54) ጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ የፈጠረ አላህ ነው፤ ከዚያም በኣርሹ ላይ ተደላደለ፤ ሌሊትን በቀን ይሸፍናል፤ ፈጥኖ ይፈልገዋል፤ ፀሐይንና ጨረቃንም ከዋክብትንም በትእዛዙ የተገሩ ሆነው (ፈጠራቸው)፤ ንቁ! መፍጠርና ማዘዝ የርሱ ብቻ ነው፤ የዓለማት ጌታ አላህ ልቅናው ጠራ። (55) ጌታችሁን በተዋረድና በድብቅ ለምኑት፤ እርሱ ወሰን አላፊዎችን አይወድም. (56) በምድርም ላይ ከበጀች በኋላ አታበላሹባት፤ ፈርታችሁና ከጅላችሁም ለምኑት፤ የአላህ እዝነት ከበጎ ሰሪዎች ቅርብ ነውና። (ሱረቱ አል-አዕራፍ፡ 54-56)
Reference: ሱራ አል-አዕራፍ ፯: ፶፬-፶፮