Loading...
Language: Amharic
وَالصَّافَّاتِ صَفًّا ﴿١﴾ فَالزَّاجِرَاتِ زَجْرًا ﴿٢﴾ فَالتَّالِيَاتِ ذِكْرًا ﴿٣﴾ إِنَّ إِلَـٰهَكُمْ لَوَاحِدٌ ﴿٤﴾ رَّبُّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا وَرَبُّ الْمَشَارِقِ ﴿٥﴾ إِنَّا زَيَّنَّا السَّمَاءَ الدُّنْيَا بِزِينَةٍ الْكَوَاكِبِ ﴿٦﴾ وَحِفْظًا مِّن كُلِّ شَيْطَانٍ مَّارِدٍ ﴿٧﴾ لَّا يَسَّمَّعُونَ إِلَى الْمَلَإِ الْأَعْلَىٰ وَيُقْذَفُونَ مِن كُلِّ جَانِبٍ ﴿٨﴾ دُحُورًا ۖ وَلَهُمْ عَذَابٌ وَاصِبٌ ﴿٩﴾ إِلَّا مَنْ خَطِفَ الْخَطْفَةَ فَأَتْبَعَهُ شِهَابٌ ثَاقِبٌ ﴿١٠﴾
ወሰ ፋቲ ሰፋ። ፈዛጂራቲ ዘጅራ። ፈታሊያቲ ዚክራ። ኢንነ ኢላሀኩም ለዋሂድ። ረቡስ ሰማዋቲ ወል አርዲ ወማ በይነሁማ ወረቡል መሻሪቂ። ኢንና ዘይንነስ ሰማአድ ዱንያ ቢዚነቲኒል ከዋኪብ። ወሂፍዘም ሚን ኩሊ ሸይጣኒም ማሪድ። ላ የሰመዑነ ኢለል መለኢል አዕላ ወዩቅዘፉነ ሚን ኩሊ ጃኒብ። ዱሁረን ወለሁም ዐዛቡን ዋሲብ። ኢላ መን ኸጢፈል ኸጥፈተ ፈአትበዐሁ ሺሀቡን ሳቂብ።
(1) በሰላፊዎች (መላእክት) እምላለሁ፤ (2) በከልካዮችም (መላእክት)፤ (3) በአንባቢዎችም (መላእክት)፤ (4) አምላካችሁ በእርግጥ አንድ ነው. (5) የሰማያትና የምድር፣ በመካከላቸውም ያለ ሁሉ ጌታ፤ የምስራቆችም ሁሉ ጌታ ነው። (6) እኛ ቅርቢቱን ሰማይ በከዋክብት ጌጥ አስጌጥናት። (7) ከአመፀኛ ሰይጣንም ሁሉ መጠበቅን (ጠበቅናት)። (8) ወደ የላይኛው ሸንጎ (መላእክት) አያዳምጡም፤ ከየአቅጣጫውም ይወረወራሉ (ይባረራሉ)። (9) ለመባረር፤ ለእነሱም ዘውታሪ ቅጣት አላቸው። (10) (ከመላእክት ንግግር) አንድን ንጥቂያ የነጠቀ ሰው ቢኖር እንጂ፤ እርሱንም ተወርዋሪ ፋና ይከተለዋል። (ሱረቱ አስ-ሷፋት፡ 1-10)
Reference: ሱራ አስ-ሳፋት ፴፯: ፩-፲